ቢሮው ለዓቃቢያነ ህግ መስጠት የጀመረውን የአቅም...

image description
- ውስጥ Laws    0

ቢሮው ለዓቃቢያነ ህግ መስጠት የጀመረውን የአቅም ግንባታ ስልጠና አጠናክሮ ቀጥሏል።

ቢሮው ለዓቃቢያነ ህግ መስጠት የጀመረውን የአቅም ግንባታ ስልጠና አጠናክሮ ቀጥሏል።

።።።።።።።

ፍትህ ቢሮ በማእከል እና በክፍለከተማ ለሚገኙ አመራሮች እና ዓቃቢያነህግ በኮንስትራክሽን ህግ፣ በአቃቢያነ ህግ ስነምግባር እና መሬት እና መሬት ነክ ህጎች ዙሪያ ለሁለተኛዙር መስጠቱን ቀጥሏል ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ  አሰፋ መብራቴ ሁለተኛውን ዙር የስልጠና መረሃግብር ባስጀመሩበት ወቅት አዲስ አበባ በከፍተኛ የእድገት ግስጋሴ ላይ ያለች ከመሆኑም ባሻገር የአለም አቀፍ የዲፕሎማቶች መቀመጫ እንደመሆኗ መጠን ተቋማችን ተመጣጣኝ የሆነ ስራ መስራት ይጠበቃል በማለት በነበረው አካሄድ በመሄድ ተወዳዳሪ ለመሆን አያስችልም ብለዋል፡፡

ሃላፊው አክለውም በየጊዜው አዳዲስ የህግ ማእቀፎች ይወጣሉ ይሻራሉ ሳይንሱም በዛው ልክ እየተሻሻለ ይገኛል ስለዚህ በምናደርገው የውል ዝግጅት፣የመንግስትና የህዝብን ጥቅም ለማስጠበቅ በምናደርገው ክርክር እንዲሁም በምናዘጋጀው የህግ ስርፀት ግንዛቤ ፈጠራ ዙሪያ የአገልግሎት አሰጣጣችን የአቃብያነ ህግ ስነ-ምግባርን ማዕከል ያደረገ መሆን ይኖርበታል ብለዋል፡፡

ዐቃብያነ ህጉ በሁለት መንገድ ራሱን ማብቃት አለበት አንደኛው ቢሮው በሚያዘጋጀው መርሃ ግብር ላይ በመሳተፍ ሌላው ዐቃቢ ህጉ በራሱ ተወዳዳሪ ለመሆን ማንበብ ከሌሎች ልምድ በመውሰድ ራሱን ማብቃት መቻል አለበት ብለው ሁሉም አቃብያነ ህግ የተዘጋጀውን የአቅም ግንባታ መርሃ ግብር በተገቢው መንገድ እንዲከታተል አሳስበዋል፡፡

የግንዛቤ ማስጨበጫው በኮንስትራክሽን ህግ ፣በዓቃቢያነ ህግ ስነምግባር እና በመሬት እና መሬት ነክ ህግ ዙሪያ ለሶስት ቀን በሁለት ዙር እንደሚሰጥ ተገልጿል።

ዛሬ በኮንስትራሽን ህግ ዙሪያ ስልጠናው መሰጠት የጀመረ ሲሆን አቶ ያዕቆብ መኩሪያ ስልጠናውን መስጠት ጀምረዋል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.