ለዐቃቢያነ ህግ፣ ዳኞች እና ለትብብር ጥምረት አባላት ስልጠና ተሰጠ።
ቀን መስከረም 15/2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ ፍትህ ቢሮ በሰው መነገድ ሰውን በህገወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር ወንጀል መከላከል ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ለዐቃቢያነ ህግ፣ለረዳት ዳኞች እና ለትብብር ጥምረት አባላት ከህይወት ኢትዮጲያ ከተባለ ግብረ ሰናይ ድርጅት ጋር በመተባበር ስልጠና ሰጠ።በሰዎች መነገድ ሰውን በህገወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር ወንጀልን ለመከላከል በወጡ ህጎች እና አለም አቀፍ እና ሃገር አቀፍ ወቅታዊ መረጃዎች ላይ ስልጠናው ተሰጥቷል።የማስተባበሪያ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ታደሰ ፈይሳ በመክፈቻ ንግግራቸው በሰው የመነገድ እና ሰውን በህገወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር ወንጀልን የህግ ማስከበር እና የወንጀል መከላከል አባላት የጋራ መረዳት እና መግባባት ኖሯቸው ለአንድ አላማ በመቆም ወንጀለኞችን ማረም በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መግባባት ለመፍጠር ያለመ ስልጠና መሆኑን ገልጸዋል።ዓቃቤሕግ አቶ ነብዩ በቀለ ወንጀሉ በአለም ዓቀፍ በአህጉር አቀፍ እና በሀገር አቀፍ ደረጃ ምን ላይ እንዳለ አመላካች ጽሁፎች አቅርበው ሰፊ ማብራሪያ የሰጡበት ሲሆን ዓቃቤሕግ ወይዘሪት ሚስጢር አፈወርቅ ህጉን እና ተጨባጭ በአዲስ አበባ በተለያየ የስልጣን እርከን ያሉ የመንግስት ተቋማት ወንጀሉን ከመከላከል እና ከመቆጣጠር አንጻር ያላቸውን ሚና መመሪያን መሰረት በማድረግ ማብራሪያ ሰጥተዋል።በመጨረሻም የጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ታደሰ ፈይሳ የህግ ማስከበር እና የወንጀል መከላከል አባላት ወንጀሉን ከመከላከል አኳያ ሕጉን ተፈጻሚ ማድረግ እንደሚጠበቅ አሳስበዋል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.