በ2017 በጀት አመት 1ኛ ሩብ ዓመት በአስተዳደ...

image description
- ውስጥ Laws    0

በ2017 በጀት አመት 1ኛ ሩብ ዓመት በአስተዳደሩ ውሳኔ ያገኙ መዛግብት  በሚደረግ ኦዲት ዙሪያ ውይይት ተደረገ።

በ2017 በጀት አመት 1ኛ ሩብ ዓመት በአስተዳደሩ ውሳኔ ያገኙ መዛግብት  በሚደረግ ኦዲት ዙሪያ ውይይት ተደረገ።
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
መስከረም28/2017
ፍትህ ቢሮ የሚከራከርባቸውና ውሳኔ ያረፈባቸውን መዛግብት ለመመርመር የፍትህ ቢሮ የበላይ አመራሩ በተገኘበት በቢሮ የህግ ኦዲትና ኢንስፔክሽን ዳይሬክቶሬት  እና የ11ዱም ክ/ከተማ ፍትህ ጽ/ቤት ኃላፊዎችን ያሳተፈ ውይይት ተደርጓል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ  ኃላፊ አቶ ተክሌ በዛብህ በአስተዳደሩ ላይ የፍርድ ቤት ውሳኔ ያረፈባቸው መዛግብትን በኦዲቱም ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እንዲቀርብ ለተሳታፊዎች መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
ኃላፊው አክለውም የባከነ የህዝብና የመንግስትን ጥቅም ለማስጠበቅ በሚረዳ መልኩ ኦዲት በልዩ ትኩረት የሚሰራ በመሆኑ የተገኙ ኃላፊዎችም ልዩ ትኩረት እንዲሰጡና በሚገኙ ግኝቶችም ዙሪያ በእያንዳንዱ ክ/ከተማ የመግቢያና የመውጫ ውይይት በማድረግ ሂደቱን ጤናማ ማድረግ ችግር ውስጥ ገብተው የተገኙ አካላትን ዓቃቤ ህጎችን ጨምሮ ሌሎች አካላትንም ለማረም እና ተጠያቂነት ለማስፈን የሚረዳ በመሆኑ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ትብብር ሊያደርጉ ይገባል ብለዋል፡፡
በፍትህ ቢሮ  የህግ ኦዲትና ኢንስፔክሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር  አቶ ታፈሰ ዘነበ እቅዱን ያቀረቡ ሲሆን የኦዲቱን አላማና ኦዲቱ የሚያተኩርባቸውን ጉዳዮች ሰፋ ባለ መልኩ ለተሳታፊዎች አቅርበዋል፡፡
በመጨረሻም በሌሎች በሚቀጥሉት ወራት ትኩረት መደረግ ባለባቸው ጉዳዮች አቅጣጫ ተቀምጦ ተሳታፊዎችም የተሰጠውን የስራ መመሪያ በመቀበል የበኩላቸውን ኃላፊነት እንደሚወጡ የጋራ መግባባት በመፍጠር መድረኩ ተጠናቋል፡፡


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.