የፍትህ አካላት በሴቶች እና ህጻናት ላይ የሚደርሰውን ጥቃት በትኩረት ሊሰሩበት ይገባል ተባለ።
የፍትህ አካላት በሴቶች እና ህጻናት ላይ የሚደርሰውን ጥቃት በትኩረት ሊሰሩበት ይገባል ተባለ።
።።።።።።።።።።።
ቀን ጥቅምት 5/2017 ዓ.ም
ይህ የተባለው በአዲስ አበባ ከተማ ፍትህ ቢሮ በሰው መነገድ ሰውን በህገወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር ወንጀል መከላከል ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ለዐቃቢያነ ህግ፣ለረዳት ዳኞች ፣ ፖሊስ እና ለትብብር ጥምረት አባላት እና መንግስታዊ ላልሆኑ ድርጅቶች በተገኙበት ሴቶች እና ህጻናትን ማዕከል ያደረገ ውይይት በተደረገበት ወቅት ነው።
በወቅቱ የማስተባበሪያ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ታደሰ ፈይሳ በመክፈቻ ንግግራቸው ሴቶች እና ህጻናትን አስመልክት በርካታ ስራዎች ተሰርተዋል ነገር ግን በሚፈለገው ደረጃ ውጤት ማምጣት አልተቻለም ብለው ችግሩ በአመለካከትም በተግባርም የሚገለጽ በመሆኑ የፍትህ አካላት ይህንን ከግንዛቤ በማስገባት ከምንጊዜውም በበለጠ ሚናቸውን ሊወጡ ይገባል ብለዋል።
በወቅቱ ሴቶች እና ህጻናትን ማዕከል ያደረጉ በአለም ዓቀፍ፣ በአህጉር አቀፍ እና በሀገር አቀፍ ደረጃ ያሉ ህጎችን አስመልክቶ ዓቃቤሕግ አቶ ነብዩ በቀለ እና ዓቃቤሕግ ወይዘሪት ሚስጢር አፈወርቅ ለውይይት አቅርበው ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተውበታል።
በሲ.ቪ.ኤ.ም ኢትዮጲያ በጎ አድራጎት ድርጅት የፍልሰት ፕሮጀክቶች አስተባባሪ የሆኑት ወይዘሪት ህይወት አሸናፊ በወቅቱ ሲ.ቪ.ኤም ኢትዮጵያ ለረጅም አመታት በሴቶችና ህጻናት ዙሪያ እደሰራ ገልጸው በቀጣይም ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በዚህ ጉዳይ እንደሚሰራ እና ድርጅቱ በዋናነት ምን ምን ጉዳዮች ላይ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን እንዲሁም በየትኞቹ ክልሎች ላይ እየሰራ እንደሚገኝ እና በቀጣይ አዳዲስ ክልሎችም አካቶ እንደሚሰራ ባጠቃላይ ከፍትህ ቢሮ ጋርም በርካታ ውጤታማ ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
በመጨረሻም የጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ታደሰ ፈይሳ የህግ ማስከበር እና የወንጀል መከላከል አባላት ወንጀሉን ከመከላከል አኳያ የህጻናት እና የሴቶች ጥቃትን የወጡ ህጎችን ተፈጻሚ ማድረግ ይጠበቃል ብለዋል ።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.