በሴቶች መብት አጠባበቅ ዙርያ ስልጠና ተሰጠ፡፡

image description
- ውስጥ Laws    0

በሴቶች መብት አጠባበቅ ዙርያ ስልጠና ተሰጠ፡፡

በሴቶች መብት አጠባበቅ ዙርያ ስልጠና ተሰጠ፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ ለሚገኙ ሰራተኞች በሴቶች ህጻናት መብት አጠባበቅ በዓለም ዓቀፍ የሰብዓዊ መብት ሰነዶችና ሀገራዊ ህጎች ላይ ስልጠና ተሰጠ፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ የሴቶችና ህጻናት ፎካል ፐርሰን የሆኑት ዐቃቢ ሕግ ዶርቃ አለሙ በመክፈቻ ንግግራቸው በሀገራችን ብሎም በከተማችን ላይ የሴቶች ጥቃት ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ጎልቶ የሚታይበት በመሆኑ የፍትህ ቢሮ ሰራተኞች ስለ ሴቶች መብት ጠለቅ ያለ እውቀት እንዲኖራቸው በተጨማሪም መብቶቻቸውን አውቀው ከሚደርስባቸው ጥቃትም ሆነ የመብት ጥሰት እራቸውን መጠበቅ  እና በሚኖሩበት ማህበረሰብ  ውስጥ ሴቶች መብቶቻቸው እንዲያውቁ እንዲያደርጉና በሴቶች ላይ የሚደርሱ ማንኛውም አይነት ጥቃት እና ጥሰቶችን የማጋለጥ እና ለመከላከልም ጉልህ ሚና የሚጫወቱ  ሰዎች  እንዲሆኑ ያደርጋቸዋል ብለዋል፡፡ 
ዐቃቢ ሕግ ራሄል አንበርብር የስልጠናውን ሰነድ ያቀረቡት ሲሆን የሴቶች መብት፣የሴቶች እኩልነት መብት፣የሴቶች መብት ከዓለም አቀፍ ህጎች አንፃር፣የሴቶች መብት በኢፌዴሪ ህገ-መንግስት፣የሴቶች መብት ከልዩ ልዩ ህጎች አንፃር ሰፋ ባለ ገለፃ አቅርበዋል፡፡
የሴቶች መብት ዓለም አቀፍ ዕውቅና የተሰጠውና በተለያዩ ዓለም ዓቀፍ ስምምነቶች ውስጥ የተደነገገ በመሆኑም እያንዳንዱ የዓለም አቀፍ ስምምነት ፈራሚ ሀገር የሴቶችን መብቶች እንዲያከብሩና እንዲያስከብሩ ኃላፊነት አለባቸው በማለት ስለ ሴቶች መብት ስልጠናውን ሰጥተዋል፡፡


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.