አመራሩ ለላቀ ተግባር መዘጋጀት አለበት።

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

አመራሩ ለላቀ ተግባር መዘጋጀት አለበት።

አመራሩ ለላቀ ተግባር መዘጋጀት አለበት።
።።።።።።።።።።
ጥቅምት 18 ቀን 2017
አቶ ተክሌ በዛብህ የፍትህ ቢሮ ኃላፊ በየደረጃው ያለ አመራር ከተለመደው አሰራር ራሱን በማላቀቅ ለላቀ ተግባር ዝግጁ መሆን አለበት ብለዋል።
ይህንን ያሉት የ2017 በጀት አመት የሩብ አመት እቅድ አፈፃፀም አመራሮችን ባወያዩበት ወቅት ነው።
በውይይቱ በዋናነት የወንጀል ጉዳይ አፈፃፀም፣ የተረቀቁ ህጎች ፣ የፍታብሔር ጉዳዩች የከተማ አስተዳደሩንና የነዋሪውን መብት ከማስጠበቅ አንፃር፣ለከተማ አስተዳደሩ ህጎችን ለማሳወቅ በሚሰሩ የስርፀት ስራዎች፣ ሰባዊ መብትን ከማስከበርና፣ በሰው የመነገድ እና ሰውን በህገወጥ መንገድ ደንበር የማሻገር ወንጀልን በተመለከተ  የነበሩ ጠንካራና ደካማ ጎኖች እና የገጠሙ ተግዳሮቶች እንዲሁም የመፍትሄ አቅጣጫ በስፋት በቢሮው የእቅድና በጀት ክትትል ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ደሳለኝ በላይ ቀርበዋል፡፡
በተያየዘም የዝግጅት ምዕራፍ ተግባርት ያሉበት ደረጃ የቢሮ ዳራይረክተሮች ቡድን በሁለት በመቧደን ክፍለ ከተሞችን ድጋፋዊ ክትትል ያደረጉበት ሪፖርት በአቶ አብዮት ጅፋራ የወንጀል ጉዳዮች ዳይሮክቶሬት ዳይረክተር በመቅረቡ በሁለቱም ገለጻዎች ሰፊ ግዘ ተወስዶበት ውይትት ተደርጎበታል፡፡
የፍትህ ቢሮ ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ ግርማ ወርቁ የተቋማት አፈጻጸም ሊለካ የሚችለው ከተማዋ እያመጣች ባለው እድገት ልክ ነው በማለት ስራዎቻችን ከዚህ አንጻር ሲታይ ተመጋጋቢ መሆን እንዳለበት ገልጸው  
ቢሮው በሚያደርጋቸው ክርክሮች ፣ የህግ ግንዛቤዎች መሰል ተግባራት ወቅታዊ የከተማ አስተዳደሩን ስራ የሚያግዝ መሆን ይኖርበታልም ብለዋል።
በመጨረሻም የፍትሕ ቢሮ ሀላፊ አቶ ተክሌ በዛብህ ፣ የፍትህ ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ አሰፋ መብራቴ እና አቶ ተስፋዬ ደጀኔ ከቤቱ በተነሱ ሀሳብ ቀጣይ አቅጣጫ ያስቀመጡ ሲሆን በሩብ አመቱ በየዘርፉ የተመዘገበው ውጤት አበረታች እንደሆነ በመግለጽ የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ርብርብ እንደሚያስፈልግ ተመላክቷል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.