
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ በሀገር አቀፍ ደረጃ የተጀመረውን የፍትህ ተቋማት ትራንስፎርሜሽን አካል የሆነውን ማህበረሰብ የፍትህ አገልግሎት ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ተካሄደ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ በሀገር አቀፍ ደረጃ የተጀመረውን የፍትህ ተቋማት ትራንስፎርሜሽን አካል የሆነውን ማህበረሰብ የፍትህ አገልግሎት ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ተካሄደ፡፡
ጥቅምት 20/02/2017
በማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ የኢፌድሬ ፍትህ ሚኒስቴር የተቋማት ግንባታና ሪፎርም ዘርፍ ሚንስትር ድኤታ ዶ/ር ኤርሚያስ የማነብርሃን፣ የፍትህ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተክሌ በዛብህ፣ የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ አይዳ አወል፣ የሔግ ኢንስቲትዩት ፎር ኢኖቬሽን ላው(HILL) መስራችና ስራስፈጻሚ ዶ/ር ሳሙኤል ሙለር እና የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ ተረሳ ስማውት እንዲሁም በየደረጃው ያሉ አመራሮችና የሃገር ሽማግሌዎች ተገኝተዋል፡፡
የፍትሕ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተክሌ በዛብህ በመክፈቻ ንግግራቸው ፍትህን እና እውነትን ፍለጋ በመንግስት ተቋማት ብቻ ታጥሮ መፍትሔ እንዲያመጣ ሲተገበር የቆየ ሲሆን የህዝቡን ነባር ባህልና ሃገር በቀል እውቀቶችን መጠቀም ባለመቻሉ በፍትህ ዘርፉ የተፈለገው ውጤት ከማምጣት ረገድ ውስንነቶች ሲስተዋል ቆየት ብለዋል፡፡
ኃላፊው አክለው ከመደበኛ የፍትህ ስርአት ውጪ በማህበረሰብ ውስጥ ያሉ አጋዥ ፍትሕ ማስገኛ መንገዶችን በመቀየስ አሰራሮችን በመዘርጋት የፍትሕ ተደራሽነትን ለማስፋት እገዛ ማድረግ አስፈልጓል፡፡
ሁሉም ግጭት ወደ ፍርድ ቤት ከመሄዱ በፊት በማህበረሰቡ የእርቅ አፈታት ዘዴዎች እና ባህላዊ የእርቅ ስርአቶችን በመጠቀም በዚህ ረገድ የሚባክነውን ኢኮኖሚ፣ ጊዜ ፣ጉልበት በመቆጠብ ማህበራዊ ግንኙነቶችን ለማጠናከር የሚረዳ ማህበረሰብ የፍትህ አገልግሎት ዛሬ ተጀምሯል መስጫ ማዕከል ተመርቆ ተከፍቷል፤ በዚህም የተጀመረውን ለውጥ ለማገዝ ምቹ መደላደልን ይፈጥራል ብለዋል፡፡
የኢፌድሬ ፍትህ ሚኒስቴር ድኤታ ዶ/ር ኤርሚያስ የማነ ብርሃን መንግስት ለውጡን ተከትሎ በርካታ ሪፎርም አድርጓል አንዱ ከፍትህ ስርአት ሲሆን በዚህም በርካታ ጥናት ተደርጓል በተለይ በመሬት፣ በውርስ፣ የቤተሰብ ግጭት የመሳሰሉት በዚህም በነበረው አካሄድ ብቻ ለውጥ ማምጣት አለመቻሉ ተረጋግጧል፡፡
በማህበረሰቡ የዳበሩ የእርቅ አፈታት ዘዴዎችን እውቅና በመስጠት ከመደበኛ ስርአት ጋር አሰናስሎ በማስኬድ የፍትህ ስርአቱን በማሻሻል ህብረተሰቡ የሚያነሳውን የፍትህ ፍላጎት ለማርካት ዛሬ ያስጀመርነውን መርሃ ግብር ውጤታማ በሆነ መልኩ እንዲካሄድ ዛሬ የተሰየሙት ሽማግሌዎች በትጋት እንደሰሩ አሳስቧል፡፡
ሒል መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ተወካዮች በበኩላቸው ፍትህ በእኩልነት መስራት በመሆኑ ተደራሽ፣ ውጤታማ መሆን አለበት በማለት ለዚህም ደግሞ መደበኛ ያልሆነው የፍትህ ዘርፍ እጅግ ጠቀሜታ አለው በማለ በርካታ ሀገራት ይህንኑ ልምድ በማራመድ ውጤታማ ሆነዋል፡፡
በመጨረሻም ማህበረሰብ የፍትህ አገልግሎት የሚያስፈፅሙ ሽማግሌዎች ተሰይመው መስሪያ ቦታ ተሰጥቷቸው ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ተጠናቋል፡፡
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.