
የህግ ጉዳይ ክርክር ዘርፍ የ1ኛ ሩብ አመት እቅድ አፈፃፀም ገመገመ፡፡
የህግ ጉዳይ ክርክር ዘርፍ የ1ኛ ሩብ አመት እቅድ አፈፃፀም ገመገመ፡፡
ግምገማውን የመሩት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትሕ ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ደጀኔ ሲሆኑ የ11ዱም ክ/ከተማ የፍትሐ ብሔር እና የወንጀል ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ተገኝተዋል፡፡
በወቅቱምክትል ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ደጀኔ በመክፈቻ ንግግራቸው ከተማ አስተዳደሩ የከተማዋን የአሰራር ስርአት ለመቀየር በስራ በተጠመደበት በአሁኑ ወቅት በሚመለከተን የስራ ድርሻ ከምንጊዜውም በላይ ከጎን በመቆም ልናግዝ ይገባል ብለው በተለይ መንግስት እያለማ ባላቸው አውታሮች ዙርያ በሚመጡ እግዶች ህጋዊነቱን በመከተል በልዩ ትኩረት መስራት ይጠበቃል ብለዋል፡፡
ኃላፊው አክለውም የግምገማ መድረኩ እግድ ከማስነሳት፣ የመንግስት ቤቶችን ከመፋለም ረገድ በነበሩ ክርክሮች በግል አቤቱታ የቀረቡ ጉዳዮችን በእርቅ ከመጨረስ፣ የደንብ ቅጣቶችን ከማስፈፀም አንፃር ግምገማው መካሄድ እንዳለበት አሳስበው አስጀምረዋል፡፡
የማዕከል እና የ11ዱም ክ/ከተማ የፍትሐ ብሔር እና የወንጀል ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት የሩብ አመት እቅድ አፈፃፀማቸውን ዝርዝር ተግባራት አቅርበው ሰፊ ውይይት ተካሄዷል፡፡
በመጨረሻ ምክትል ኃላፊው አቶ ተስፋዬ ደጀኔ ከቤቱ ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ በመስጠት ኮሪደር ልማቱ ጋር ተያይዞ የሚቀርቡ ህግ ነክ ጉዳዮችን አፋጣኝ ምላሽ መስጠት ፣ ከፖሊ ጋር በቅንጅት በመስራት የዜጎችን የሰብአዊ መብት አያያዝ ስርአትን ማስጠበቅ የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ መሆኑን አስቀምጠዋል፡፡
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.