
ሕግ ማስከበርና ወንጀል መከላከል ስራ ቡድን በተጎጂዎችን ቅብብሎሽ ስርአት እና ወንጀለኞች ተጠያቂነት ዙሪያ ለፍትህ አካላት ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ተጠናቀቀ።
ሕግ ማስከበርና ወንጀል መከላከል ስራ ቡድን በተጎጂዎችን ቅብብሎሽ ስርአት እና ወንጀለኞች ተጠያቂነት ዙሪያ ለፍትህ አካላት ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ተጠናቀቀ።
።።።።።።።
ስልጠናው በፍትሐብሔር ስነስረዓት ህግ፣ በደንብ ቁጥር 126/2014 እና መመሪያዎች፣በተጎጂ ቅብብሎሽ ሰነድ፣ አለም አቀፍ እና ሀገር አቀፍ ደረጃ ባሉ የህግ ማዕቀፎች ዙሪያ ሲሆን የአዲስ አበባ ፍትህ ቢሮ በሰው የመነገድ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ከ IOM አለም አቀፍ ተቋም ጋር በመተባበር አዘጋጅቷል ።
በስልጠና መድረኩ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የይግባኝ ሰሚፍርድ ቤት ሰብሳቢ ዳኞች የክፍለ ከተማ ምድብ ችሎት ሰብሳቢ ዳኞች፣ የክ/ከተማ ፍትህ ጽ/ቤት ኃላፊዎች እንዲሁም የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን መርማሪዎች ተሳትፈዋል።
በተለያዩ ርዕሴ ጉዳዮች የስልጠና ሰነዶችን ዓቃቢያነ ህግ አቶ ነብዩ በቀለ ፣ አቶ ናሆም ሰለሞን፣ ወይዘሮ መኪያ ዲኖ እና ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ዳኛ ጊዮን መስፍን እንዲሁም የIOM ባለሞያ ወይዘሮ ፈትያ መሐመድ አቅርበዋል።
ወንጀሉን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር በቅንጅት መስራትን ይጠይቃል ያሉት በሰው መነገድና በሕገወጥ ድንበር የማሻገር ወንጀል መከላከል የማስተባበሪያ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ታደሰ ፈይሳ የወንጀሉ ተጎጂዎችን መልሶ በማቋቋም እና በማጠናከር የቅብብሎሽ ስርዓቱ ተጠያቂነት ለማስፈን የፍትህ አካላት ሚና ከፍቸኛ እንደሆነ አንስተዋል።
የማስተባበሪያ ጽ/ቤት ኃላፊ ተጎጂዎችን መልሶ ከማቋቋም ረገድ የቅብብሎሽ መመሪያ አስፈጻሚ ተቋማት ሀላፊነታቸውን መወጣት እንዳለባቸው እና በማይወጡት ላይ ተጠያቂነት እንደሚያስከትልም አስገንዝቧል።
ሰልጣኞች መሰል አጋዥ እና ወቅታዊ የግንዛቤ መድረኮች የሚያበረታቱና የስራ ሞራልን የሚያነቃቁ ናቸው በማለት አዘጋጅ ክፍሉ እውቅና ሰጥተዋል።
በመድረኩ ማጠቃለያ ተገኝተው የትኩረት ነጥቦችን ያነሱት የአዲስ አበባ ፍትህ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተክሌ በዛብህ ሲሆኑ በሰው የመነገድ ወንጀል መከላከል መቆጣጠር ለፍትህ አካላት ብቻ የተተወ የግባር ባይሆንም በሕግ ተቆጥሮ የተሰጠንና ካልተወጣን የሚንጠየቅበት እንደሆነ በማብራራት ለተጠያቅነት ብለን ብቻ ሳይሆን የዜጎች ሕይወትና ደህንነት፣ የሀገር ሰላምና ደህንነት ብሎም ገጽታ መበላሸት እንደ አንድ ዜጋ ሊያሳስበን የሚገባ የሕልውና ጉዳይ ጭምር ስለመሆኑ በማንሳት የተጀመሩ ተግባራትን ተቋማዊ አድርጎ የመምራትና ከተለመደው መንገድም ወጣ ባለ መላው ሕዝብን ባሳተፈ መንገድ ትግል መደረግ እንዳለበት አሳስበዋል
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.