የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ የህግ...

image description
- ውስጥ Laws    0

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ የህግ ስርፀት ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት ስልጠና በሁለት ዙር ለአስፈጻሚ ተቋማት ስልጠና ሰጠ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ የህግ ስርፀት ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት ስልጠና በሁለት ዙር ለአስፈጻሚ ተቋማት ስልጠና ሰጠ።

።።።።።።።።።።።።።።።

23/02/2017 ዓ.ም

 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትሕ ቢሮ ከፐብሊክ ሰርቪስ ሰው ኃብት ልማት ቢሮ ጋር በመተባበር በፌድራል አስተዳደር ሥነ-ሥርዓት አዋጅ ቁጥር 1183/2012 ላይ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሥራ አመራር አካዳሚ ከከተማ አስተዳደሩ አሰፈፃሚ ተቋማት ለመጡ 500 ዳይሬክተር እና ቡድን መሪዎች ስልጠና ሰጠ።

ስልጠናው በማዕከል እና በክፍለ ከተማ በመጡ ዐቃቢያነ ሕግ ስልጠናው የተሰጠ ሲሆን በስልጠናው በአዋጁ በዋናነት በተዋቀረባቸው ሶሰሰቱ ምሶሶዎች ማለትም የመመሪያ አወጣት ሥርዓት፣ አስተዳደራዊ ውሳኔ አሰጣጥ ሥርዓት እና የፍርድ ቤት ክለሳ ሥርዓት ላይ በማተኮር የተሰጠ ስልጠና ነው፡፡

 

ተቋማት በእናት ህጋቸው ወይም በሌላ ህግ መመሪያ የማውጣት ስልጣን ሲሰጣቸው ብቻ መመሪያ ማውጣት እንደሚችሉ መመሪያ ማውጫ ጊዜ በተመለከተ መመሪያ ማውጣት በአስገዳጅ በሆነ ሁኔታ ሲደነነገግ ተቋማት መመሪያ ማውጣት ያለባቸው በሶስት ወራ ጊዜ ሲሆን አስገዳጅ ባልሆነ ሁኔታ በተደነገገ ጊዚ መመሪያ በተገቢው ጊዜ ማውጣት እንዳለባቸው፤ የቅድመ መመሪያ አወጣጥ ሥነ-ሥርዓት በስልጠና ሰነዱ በዝርዝር በማብራሪያ ለሰልጣኞች የቀረበ ሲሆን የሚወጡ መመሪያዎች ሚመለከታቸው ባለድርሻ አስተያየት እንዲሰጡበት የመመሪያው ረቂቅ በመላክ አስተያየት እንዲሰጡበት ከአስራ አምስት ቀን ያላነሰ ጊዜ መስጠት እንዳለባቸው እና በአስፈፃሚ ተቋማት የሚወጡ መመሪያዎች በሙሉ መመዘገብ እንዳለባቸው ያልተመዘገ እና በተቋሙ ድህረ ገጽ ላይ ያልተጫነ መመሪያ ተፈፀሚነት እንደማይኖረው፤

አስተዳደራዊ ውሳኔ የሚሰጠው ሰው የአስተዳደር ተቋሙ የበላይ ኃላፊ ወይም  ወይም ስልጣን የተሰጠው የተቋሙ የስራ ኃላፊ ወይም ሠራተኛ ብቻ መሆን እንዳለበት፤ አስተዳደራዊ ውሳኔ ጥያቄ አቀራረብ፣ ጥያቄውን አቀባበል ጉዳዩን መስማት በአዋጁ በተደነገገው መርሆዎች በመከተል ብቻ መሆን እንዳለበት፤

በአስፈፃሚ ተቋማት የወጡ መመሪያዎች እና አስተዳደራዊ ውሰኔዎች በፍርድ ቤት እንደሚከለስ በፍርድ ቤት የአስተዳደር መመሪያ ሲሆን  የክለሳ ምክኒያቶች አንደኛ አዋጅ ክፍል ሁለት የተመለከቱትን የሥነ-ሥርዓት ድንጋጌዎች ሳይከተል የወጣ መሆኑ ሲረጋገጥ፤ ሁለተኛ ከአስተዳደር ተቋሙ የሥልጣን ገደብ ውጪ የወጣ ሲሆን፤ ሶስተኛ በእርከን ከመመሪያ በላይ ከሆኑ ሌሎች ህጎች የሚቃረን ሲሆን ነው፡፡ እንዲሁም አስተዳደራዊ ውሳኔ ክላሳ ምክንያት አዋጅ ክፍል ሦስት የተደነገጉትን መርሆዎች የጣሰ ሲሆን እንደሆነ፤ እና የፍርድቤት ክላሳ በማን እንደሚቀርብ የአስተዳደር መመሪያ እና ውሳኔ ክለሳ ማየት የሚችሉ ፍርድ ቤቶች እና የሚቀርብበትን ጊዜ በመግለጽ ሰፊ ገለፃነ ማብራሪያ የተሰጠባቸው ጉዳዮች ናቸው፡፡

በመጨረሻም  ከሰልጣኞች ለቀረቡ ጥያቄዎች በአሰልጣኞች ሰፊ ማብራሪያ እና ገለፃ በመስጠት ስልጠናው ተጠናቋል፡፡


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.