የፍትህ ቢሮ 2017 በጀት አመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የፍትህ ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ አፈፃፀም በምክርቤት ተገመገመ
የፍትህ ቢሮ 2017 በጀት አመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የፍትህ ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ አፈፃፀም በምክርቤት ተገመገመ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ምክርቤት ምክትል አፈጉባኤ አዲስ አበባ ከተማ እጅግ እያደገችና እየዘመነች ያለች ከተማ በመሆኗ ቢሮዎች በዛ ደረጃ መዘመንና የሕዝብ አገልግሎት ማሳለጥ አለባቸው በማለት በፍትህ ቢሮ ያለው ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ አፈፃፀም በሪፖርት ስንገመግም የተሻለ በመሆኑ በተጨባጭ ያለውን መሻሻል በአካል መመልከትና ድጋፍ ማድረግ በማስፈለጉ መድረክ መመቻቸቱን ገልጸዋል፡፡
ምክትል አፈ-ጉባኤ የፍትህ ዘርፍ ትራንስፎርሜሽን የደረሰበትን የአደረጃጀትና አሰራር፣ አገልግሎት አሰጣጥ ፣ ቴክኖሎጅ አጠቃቀም ፣ ግብዓት የመሳሰሉ በተመለከተ ከታቀዱት ምን ተከናወነ እንዲሁም ምን ተግዳሮት አለ የሚለውን በማየት የጋራ መፍትሔ ለማምጣት አስፈላጊ ነው ብለዋል ፡፡
በወቅቱ የአዲስ አበባ ከተማ አአስተዳደር ፍትህ ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ አሰፋ መብራቴ ቢሮ 2017 ዓ.ም የሩብ ዓመት ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ አፈፃፀም ባቀረቡበት ወቅት የፍትህ ዘርፍ አመራሮችና ባለሙያዎችን የማጥራት ስራ ትኩረት መሰጠቱ ፣ ማህበረሰብ አቀፍ ፍትህ አገልግሎት ማስጀመር መቻሉ፣ አገልግሎት ሰጭ ተቋማትነን የህግ ማዕቀፍ እንድኖራቸው መደረጉ ፣ ስራዎችን በቴክኖሎጅ ማዘመን መቻሉ፣ የህግ ተደራሽነትን ለማስፋት ተጨማሪ ተክኖሎጅ መጠቀም መቻሉ በሩብ ዓመቱ መፈፀም መቻሉ ገልፀዋል ፡፡
የምክርቤት አመራሩና አባላት ከቀረበው አፈፃፀም ተነስተው ሀሳብ አስተያየት ፣ጥያቄዎችን በማንሳት በስፋት ተወያይተውበታል፡፡
የፍትህ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተክሌ በዛብህ የተከበሩ የምክር ቤት አባላት ስራዎች ምን ደረጃ ላይ እንዳሉ ለማየት መምጣታቸውን በማመስገን ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ በሰጡበት ወቅት በተለይ በቴክኖሎጅ ተደግፈው በሚሰጡ አገልግሎቶች ፣ ወደ ፍርድ ቤት የሚሄዱ የግለሰብ ጉዳዮችና ዝቅተኛ ወንጀል ድርጊቶች በመግባባት እንዲያልቅ ከማድረግ አንፃር ፣ ንቃተ ህግን ተደራሽ ከማድረግ አ ንፃር የተሰሩ ስራዎች ላይ ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
በመጨረሻም ምክትል አፈ-ጉባኤዋ ፍትህ ትራንስፎርሜሽን እቅድ ትግበራ ያየንበት መንገድ ግልፅና ትክክለኛ ስዕል የያዝንበት ነው በማለት በተለይ ቢሮውን ለመቀየር የተሄደበት መንገድ የሚበረታታ ነው በማለት በቀጣይ መደገፍ ባለባቸው ጉደዮች ላይ አቅጣጫ ሰጥተው ከመጡት ሉካን ቡድን ጋር ቢሮው በአካል በመንቀሳቀስ ምልከታ አድርገዋል፡፡
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.