በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 56/2010 ዓ.ም ስልጠና ተሰጠ፡::
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 56/2010 ዓ.ም ስልጠና ተሰጠ፡::
ጥቅምት 26/2017
ስልጠናው በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ የሰብአዊ መብት ድርጊት መርሃ ግብር ጽ/ቤት የተዘጋጀ ሲሆን የቢሮው ሰራተኞች ተሳትፈውበታል፡፡
የስልጠናውን የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሰብአዊ መብት ድርጊት መርሃ ግብር ጽ/ቤት ሃፊ የሆኑት አቶ ግዛው አጥናፉ እንዳሉት የሰብአዊ መብት ለሰው ልጆች ከተሰጡ መብቶች ግዙፉ መብት መሆኑን ገልጸው ስነምግባር ለአንድ የመንግስት ሰራተኛ አስፈላጊ መሆኑን እና ስልጠናውን በአግባቡ መከታተል እንዲችሉ በመግለፅ ስልጠናውን አስጀምረዋል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ ዐቃቢ ህግ የሆኑት አቶ ደጉ የኔነው ስልጠናውን የሰጡ ሲሆን የመንግስት ሰራተኛ መብትና ግዴታን፣ በአዋጅ ቁጥር 56/2010 ዓ.ም አንቀፅ 70 እና የአስተዳደር የዲሲፕሊን አወሳሰድ ፣ ስለ ቅሬታ ምንነት አቀራረብ ፣ስለዲስፕሊን ኮሚቴ አወቃቀር ፣ስለ ቀላልና ከባድ የዲስፕሊን ቅጣት፣እርምጃ አወሳሰድ፣የመሳሰሉትን በተበብራራና ግልፅ በሆነ መንገድ አቅርበዋል፡፡
የጽ/ ቤቱ ዐቃቢ ህግ የሆኑት ወ/ሮ ሰላማዊት በላቸው ሰራተኛው መብትና ግዴታውን የሚያውቅበት በደንብና በመመርያ የሚሰራበት ስለሆነ ሰራተኛው መብትና ግዴታውን መለየት እንዳለበትና ግንዛቤ እንዲኖራችሁ የተዘጋጀ መሆኑን ገልፀው በቀጣይ እንዲህ ያለ ስልጠናዎች ይቀጥላሉ በማለት ስልጠናውን የሰለጠኑትን ሰራተኞች አመስግነዋል፡፡
በመጨረሻም የስልጠናው ተሳታፊዎች የተለያዩ ጥያቄዎች አስተያየቶች ና ሃሳቦችን በማንሳት ለተነሱት ጉዳዮች የሚመለከተው አካል ምላሽ በመስጠት ስልጠናው ተጠናቋል፡፡
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.