የሆቴል ባለሙያዎችን አለባበስ እና የመዋቢያ ጌጣ...

image description
- ውስጥ Laws    0

የሆቴል ባለሙያዎችን አለባበስ እና የመዋቢያ ጌጣጌጥ አጠቃቀም ሥርዓት የሚወስን  ደንብ ወጣ፡፡

የሆቴል ባለሙያዎችን አለባበስ እና የመዋቢያ ጌጣጌጥ አጠቃቀም ሥርዓት የሚወስን  ደንብ ወጣ፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ይህ ደንብ ቁጥር 178/2017 ሆኖ የወጣ ሲሆን በሆቴልና መሰል አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ውስጥ ለሚሰሩ ባለሙያዎች ወጥ የሆነ የአለባበስ፤የጌጣጌጥ እና የመዋቢያ አጠቃቀም ሥርዓት በመዘርጋት የሀገር ባህልና እሴት እንዲጠበቅ ለማድረግ የወጣ ደንብ ነው፡፡ 
ከደንቡ የአለባበስ ስርአት ውስጥ ለአብነት ደረት ክፍልን ያልሸፈነ ወይም ከአንገት በታች ያለውን የሰውነት ክፍል የሚሸፍን ሸሚዝ ያለበሰ፤የሴቶች ጉርድ ቀሚስ ቁመቱና ቅዱ ከጉልበት በላይ ከሆነ፤ ከጋብቻ ቀለበት ውጪ ጌጣጌጦችን በሚታዩ የሰውነት ክፍሎች ላይ ከተደረገ እንደሚያስቀጣ ያስቀምጣል፡፡
ደንብ ቁጥር 178/2017 በዘርፉ ተሰማርተው የሚሰሩ ሙያተኞች ሊደርስባቸው ከሚችለው አካላዊ፤ሥነ-ልቦናዊ ጫና እና አላስፈላጊ ጥቃቶችን ለመከላከል ብሎም  በከተማው የሚሰጠው የሆቴል አገልግሎት ዓለም አቀፍ መስፈርትን የሚያሟላ እንዲሆን ማድረግ ነው፡፡
ይህ ደንብ በሆቴልና መሰል አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የተሰማራ ባለሙያ በደንቡ በተደነገገው መሰረት አክብሮ እየሰራ ስለመሆኑ ወቅቱን የጠበቀ ክትትል የሚደረግ ሲሆን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባህል፣ኪነጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ከአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ኮሚሽን እና የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ጋር በቅንጅት በመስራት ደንቡ ተፈጻሚ እንዲሆን ይደረጋል፡፡


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.