"ሃገራዊ መግባባት ለህብረ ብሄራዊ ለአንድነት"

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

"ሃገራዊ መግባባት ለህብረ ብሄራዊ ለአንድነት"

"ሃገራዊ መግባባት ለህብረ ብሄራዊ ለአንድነት" ህዳር 11/2017 ቢሮው 19ኛውን የብሄሮች እና ብሄረሰቦች ቀንን አከበረ ፡፡ በክብረ በዓሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ደጀኔ የመክፈቻ ንግግር እና የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ባደረጉበት ወቅት የአብሮነትና ችግሮችን የመፍታት ጠንካራ ባህል ያለን ህዝቦች በመሆናችን ብዝሃ ማንነታችን አንድነታችን እና ኩራታችን ሆኖ ለብዙ አመታት ኖረናል ዛሬ በዓሉን ስናከብር ከትላንትናው ምን ተማርን ዛሬ ላይ ምን እንስራ ነገን ለመስራት ምን እናቅድ በሚል የምናከብረው በዓላችን ነው ብለዋል ኃላፊው አክለው ሃገራችን ኢትዮጵያ ሰላሟ የተጠበቀ፣ የበለጸገች ሃገር፣ የህግ የበላይነት የተረጋገጠባት ሃገር ለማድረግ ሁላችንም የበኩላችንን ማድረግ ይጠበቅብናል ብለው ህገ መንግስቱ ለኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች ፣ ሃይማኖቶች ባጠቃላይ ለብዝሃ ማንነት እውቅና የሰጠ ነው ብለዋል፡፡ በወቅቱ ለፓናል ውይይቱን ያቀረቡት ሰነድ ዐቃቢ ሕግ ወ/ሮ ራሄል አንበርብር ስለ ፌደራሊዝም ጠቅላላ መገለጫዎችና የሀገራት ልምድ፣ የኢትዮጵያ ፌደራል ስርአት ገፅታዎች እና የህብረ ብሔራዊ ፌደራላዊ ስርአታችንን ግንባታ እያጋጠሙት ያሉ ተግዳሮቶችና የመፍትሔ ሃሳቦች በማቅረብ "ሃገራዊ መግባባት ለህብረ ብሄራዊ ለአንድነት" በሚል መሪ ቃል የፌደራል ስርአት ፣ ባህርያት ፣ ስኬት ፣ ተግዳሮትና መፍትሄ ላይ ያቀረቡ ሲሆን ዓቃቢ ህጓ ሁሉም በቂ ግንዛቤ በመያዝ የራሱን ሚና እንዲጫወት ያስፈልጋል በማለት አሳስበዋል፡፡ በመጨረሻ በቀረበው የፓናል ውይይት ሰነድ ሰፊ ውይይት የተደረገ ሲሆን በዓሉን አስመልክቶ የተለያዩ የብሔር ብሔረሰቦች ቋንቋ ተናጋሪዎች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈው በተለያዩ ደማቅ ሁነቶች ተከብሮ ውሏል፡፡

Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.