ማስተባበሪያ ጽ/ቤቱ ለቢሮ ሰራተኞች ስልጠና ተሰ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ማስተባበሪያ ጽ/ቤቱ ለቢሮ ሰራተኞች ስልጠና ተሰጠ፡፡

ማስተባበሪያ ጽ/ቤቱ ለቢሮ ሰራተኞች ስልጠና ተሰጠ፡፡

፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡

ህዳር 12/2017 /ፍትህ ቢሮ/

 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትሕ ቢሮ በሰው የመነገድ ሰውን በህገ ወጥ ድንበር ማሻገር ወንጀል መከላከል ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ለሰራተኛው በሰው መነገድ ሰውን በህገወጥ መንገድ ድንበር መሻገር ወንጀልን አስመልክቶ በወጡ ድንጋጌዎች ዙሪያ ስልጠና ሰጠ። ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ታደሰ ፈይሳ ቀመክፈቻ ንግግር ህገ ወጥ የሰዎች ዝውውር አስከፊ ገጽታ ያለው አለማቀፋዊ ችግር ነው ብለው የቢሮው ሰራተኞች የወጡትን የህግድንጋጌዎች ላይ ግንዛቤ  እንዲኖራችሁ እና ወንጀሉን በትብብር ጥምረት ለመከላከል እንዲያስችል ስልጠናው አስፈልጓል ብለዋል፡፡

ስልጠናውን የሰጡት ዐቃቢ ሕግ ወ/ሮ ራሄል አንበርብር ሲሆኑ በሰው የመነገድ እና ሰውን በሕገ-ወጥ መንገድ ድንበር የማሻገር ወንጀል የወጣ አዋጅ ቁጥር 1178/2012 እና ሰውን በህገወጥ መንገድ ለስራ ወደ ውጭ ሀገር መላክ ወንጀሎችን በማቅረብ የወንጀሉን ምንነት ፣አለም አቀፍና ሀገር አቀፍ የህግ ማዕቀፎችን ማየት ፣ፖሊሲዎች ፣ሌሎች በዚህ አዋጅ የተሸፈኑ ወንጀሎች ፣የወንጀል መከላከል ፣የተጎጂዎች እንክብካቤና መልሶ ማቋቋም ፣የትብብር ማዕቀፎች ላይ ሰነድ በማቅረብ የስልጠናዉ ተሳታፊዎች የወንጀሉን ምንነት እንዲሁም በሀገርና በከተማችን የልማት እንቅስቃሴ ላይ የሚያስከትለው ትልቅ ጉዳት ለማስገንዘብ ፣ እያንዳንዱ ተሳታፊ የችግሩን አሳሳቢነት ተረድቶ ከትብብር ጥምረቱ ተልዕኮ ጋር በማቀናጀት መፍትሔ ሰጪ እንዲሆን ለማስቻል ዓላማውን ገልፀዋል፡፡

የጽ/ቤት ኃላፊው አቶ ታደሰ ፈይሳ የትብብር ጥምረቱ አደረጃጀትና የተቋቋመበት ዋና አላማና  ፋይዳዎች ላይ ማብራሪያ በመስጠት በተደራጀ መንገድ ችግሩ የሚቀረፍበት ህጋዊ የውጭ ሀገር ስራ ስምሪት እንዲጎለብት በቅንጅት ውጤታማ ወንጀል መከላከል እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡

በመጨረሻም ከቤቱ ለተነሱት አስተያየት እና ጥያቄ ምላሽ በመስጠት ሁሉም የማህበረሰብ ክፍል በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ባለቤት እንዲሆኑ እና ህገ ወጦችን እንዲያጋልጡ ጠይቀዋል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.