የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትሕ ቢሮ በክረ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትሕ ቢሮ በክረምት ወራት የተከላቸውን ችግኝ የመንከባከብ መረሀ ግብር አከናወነ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትሕ ቢሮ በክረምት ወራት የተከላቸውን ችግኝ የመንከባከብ መረሀ ግብር አከናወነ። ።።።።።።።።።።።።። ህዳር 25 ቀን 2017 በመረሀ ግብሩ የፍትህ ቢሮ አመራሮች ሰራተኞች እንዲሁም በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 አመራሮች እና ሰራተኞች ተገኝተዋል። በወቅቱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተክሌ በዛብህ በ2016 በጀት አመት በሀገር አቀፍ ብሎም በከተማ ደረጃ የተካሄደውን የአረንጓዴ አሻራ ልማት መርሀ ግብር ተግባራዊ አድርገናል ብለው ዛሬ ደግሞ ችግኞቹ እንዳይደርቁ ባስቀመጥነው መረሀ ግብር መሰረት ውሃ የማጠጣት እንክብካቤ በማድረግ ሀላፊነታችን እየተወጣን እንገኛለን በማለት ችግኞችን መትከል ብቻ ሳይሆን ተንከባክቦ የጽድቀት መጠናቸውን ከፍተኛ የማድረግ ኃላፊነት ጭምር በመሆኑ ቀጣይነት ባለው መልኩ ችግኞቹን እየተንከባከብን እንሄዳለን ብለዋል፡፡

Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.