የወጡ ሕጎችን ከማስረጽ እና ሕጎች ተፈጻሚነት ከመከታተል አንጻር ከእቅድ ባሻገር መረባረብ እንደሚገባ ተጠቆመ
የወጡ ሕጎችን ከማስረጽ እና ሕጎች ተፈጻሚነት ከመከታተል አንጻር ከእቅድ ባሻገር መረባረብ እንደሚገባ ተጠቆመ።
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ህዳር 20 ቀን /2017
የወጡ ሕጎችን የማስረጽ፣ መንግስት ተቋማት የሚዋዋሉ ውሎች እና ሕጎች ተፈጻሚነት ዙሪያ ትኩረት ያደረገ ምክክር የተደረገ ሲሆን ከማዕከል እስከ ክ/ከ የህግ ስርፀትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት ዳይረክተሮችና ባለሙያዎች ተሳትፎቶበታል። በመድረኩ አስተዳደራዊ ውሳኔ ህጋዊነትን፣ በከተማ አስተዳደሩ የወጡ ህጎች ተፈፃሚነት፣ የውል ህጋዊነትን ከማረጋገጥ እና በአስፈፃሚ ተቋማት ለሚገኙ የህግ አገልግሎት ክፍሎች ክትትልና ድጋፍ ከማድረግ አንጻር ዝርዝር ተካሂዷል፡፡
የፍትህ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተክሌ በዛብህ በመክፈቻ ንግግራቸው በዘርፉ እቅድን መነሻ በማድረግ የተመዘገቡ ውጤቶች አመርቂ ቢሆንም ከህብረተሰቡ ፍላጎት አንፃር አቃቢ ህጉም ሆነ አመራሩ አንድ ደረጃ ከፍ ያለ ስራ መስራት ይጠበቃል ብለው አቃብያነ ህጉ በከተማ አስተዳደሩም ሆነ በፌደራል መንግስቱ የወጡ ህጎችን በተገቢው በመረዳት ተደራሽ በማድረግ የፍትህ አገልግሎቱን በሚፈለገው ልክ ማረጋገጥ ከምንግዜውም በበለጠ መፍጠን ይጠበቃል፡፡
በወቅቱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትሕ ቢሮ የህግ ስርፀትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት አቶ ሙሴ አንበሴ በአንደኛ ሩብ አመት የስራ ክፍሉን አፌጻጸም ያለበትን ደረጃ በተለይም ከምክር ቤት ፣ ከፕላንና ልማት ቢሮ፣ ከፍትህ ቢሮ በተሰጡ ግብረመልሶች መነሻ ለውይይቱ መነሻ የሚሆን ገለፃ ቀርበው በርካታ ሐሳቦች በተሳታፊዎች ተነስቷል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ አሰፋ መብራቴ ምክክሩን ሲያጠቃልሉም አዋጅ ቁጥር 1183/2012 መሰረት በተቋማት ለሚደረግ የአስተዳደራዊ ውሳኔ አሰጣጥ ከአዋጅ፣ ደንብና መመሪያ መሠረት ውሳኔ ስለመስጠት አለመስጠቱ እንዲሁም የሚሰጡ ውሳኔዎች በፍትህ ሚኒስቴር በተመዘገቡ መመሪያዎች መሠረት መሆን እንደሚገባ ተገልጿል፡፡
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.