የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ የ2017 በጀት አመት የ4 ወራት እቅድ አፈፃፀም ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አደረገ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ የ2017 በጀት አመት የ4 ወራት እቅድ አፈፃፀም ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አደረገ።
።።።።።።።።።።።።
በውይይቱ የአዲስ አበባ ሰላም ፍትህ እና መልካም አሰተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ፣ በፍትህ ቢሮ በየደረጃው ያሉ አመራሮች ፣በከተማ አስተዳደሩ ያሉ የቢሮዎችና ተቋማት ኃላፊዎች እና ተወካዮቻቸው በተገኙበት በቀን 1/4/2017 ተካሂዷል።
የአዲስ አበባ ፍትህ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተክሌ በዛብህ በከተማ ደረጃ ተቋማትን ወክለን በፍ/ቤቶች ስንከራከር በበርካታ መዛግብት ያሸነፍን ቢሆንም በተወሰኑ መዝገቦች የተረታንባቸውን ምክንያቶችን በመለየት ኦዲት በማድረግ የክርክር ሂደቱ ፣የመረጃ እንዲሁም ከተቋማት ጋር ባለ የአሰራር ክፍተት እንደሆነ የመለየት ስራ መሰራቱን ገልጸው የቅንጅት ስራው ያለበትን ደረጃ አውቆ ቀጣይ እርምጃ ለመውሰድ ውይይት ማድረግ እንዳስፈለገ ገልጸዋል።
ኃላፊው ቢሮው ያለው ውስን የሆነውን የመንግስትን እና የህዝብን ሀብት ለማስጠበቅ በትኩረት እየተሰራ ነው በማለት ተቋማት በተለይ የመንግስትና የህዝብን ጥቅም የሚያሳጡ ሀላፊነት የጎደላቸው ተግባራት ሲፈፀም ህጋዊ እርምጃ መወሰድ እንደሚጠበቅባቸውና ተጠያቅነት ስርዓት በተገቢው ማስፈን እንደሚያስፈልግ አሳስቧል።
በአዲስ አበባ ምክርቤት የሰላም ፍትህና መልካም አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ሙሉነህ ደሳለኝ ተቋማት እንዴት ተናበው እና ተቀናጅተው ይሰራሉ በሚል ምክርቤቱ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል በማለት ፍትህ ቢሮ ክትትል በምናደርግበት ወቅት ከጊዜ ወደጊዜ ለውጥ እያሳየ የመጣ ተቋም ነው ብለው በተለይ ከፍታብሔር እና ከወንጀል ክርክሮች አንጻር፣ ሕጎችን በጥራት ከማርቀቅና ተቋማትን ከህግ አንጻር ከማማከር ያለው መሻሻል አበረታች ነው።
በሪፖርቱ በዋናነት ፣ በወንጀል ጉዳዮች አፈፃፀም፣ በተረቀቁ ህጎች ፣ በፍታብሔር ጉዳዩች የከተማ አስተዳደሩንና የነዋሪውን መብት ከማስጠበቅ አንፃር፣የመንግስት ተቋማት መካከል የሚነሱ የፍታብሔር አለመግባባቶች፣ ለከተማ አስተዳደሩ ህጎችን ለማሳወቅ በሚሰሩ የስርፀት ስራዎች ፣በሰው መነገድ እና ሰውን በህገወጥ መንገድ ደንበር የማሻገር ወንጀልን በተመለከተ የነበሩ ጠንካራና ደካማ ጎኖች እንዲሁም የገጠሙ ችግሮች የመፍትሄ አቅጣጫ በስፋት በፍትህ ቢሮ የወንጀል ጉዳዮች ዳይረክተር በሆኑት በአቶ አብዮት ጂፋራ ከሰፊ ማብራሪያ ጋር ቀርቧል።
የቢሮ ምክትል ሃላፊ አቶ ተስፋዬ ደጀኔ በበኩላቸው ቢሮው በአወጅ ከተሰጡት ዋነኛው ለከተማ ከስተዳደሩ የህግ አማካሪ ሆኖ መስራት ነው በማለት በዚህም ተቋማት ሲከሰሱ ወክሎ በፍርድ ቤት መከራከር፣ በከተማ አስተዳደሩ ተፈጻሚነት ያላቸውን ህጎች የማስረጽ እና ህጎችን የማርቀቅ ስራዎችን በትጋት እየሰራ እንደሚገኝ አንስቶ ይህንን የሚሸከም ተቋም ለመገባት ዐቃቢያነ ህጉን በብቃት የማደራጀት በተለይ ስነምግባርን ማዕከል ያደረገ የአቅም ግንባታ በመስጠት ለክርክር የቀረቡ መዝገቦች አስቀድሞ ኦዲት ለማድረግ የአሰራር ስርአት በማበጀት ተቋም እየገነባን እንገኛለን ብለዋል።
አቶ ተስፋዬ አክለው ከተቋማት ጋር ቅንጅታዊ አሰራር በመዘርጋት ህጋዊ ሆነን ስንሰራ የሚገጥሙ ተግዳሮቶችን መቅረፍ ያስፈልጋል ብለው በቀጣይ አስጠቂ መስረጃዎችን ፣ወቅቱን ያልጠበቀ መረጃዎችን ባለመላክ እና ለምስክርነት የማቀርቡ አካላት ላይ ተቋማት ክትትል በማድረግ እንድንተባበር እና ተቀናጅተን የመንግስትን እና የህዝብን ሀብት እንታደግ በማለት አሳስበዋል።
በውይይቱ ተሳተፊዎች ፍትህ ቢሮ በ4 ወሩ ቀደም ሲል ከነበረው በተሻለ ጥሩ አፈፃፀም እንዳከናወነ ፣ተቋማትን እየደገፈ ያለበት ሁኔታ ይበል የሚያሰኝ እንደሆነ ተነስቷል ።
በማጠቃለያው በአዲስ አበባ ምክርቤት ሰላም ፍትህና መልካም አስተዳደር ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ሙሉነህ ደሳለኝ የፍትህ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተክሌ በዛብህ እና ምክትል የቢሮ ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ደጀኔ ለተነሱት ጥያቄዎች ምላሽ በመስጠት ዉይይቱ ተጠናቋል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.