የፕሮጀክት አፈፃፀም ምልከታ በማድረግ ተገመገመ፡...

image description
- ውስጥ Laws    0

የፕሮጀክት አፈፃፀም ምልከታ በማድረግ ተገመገመ፡፡

የፕሮጀክት አፈፃፀም ምልከታ በማድረግ ተገመገመ፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
9/04/2017 
ግምገማው የተደረገው ከጣልያን በመጡ የፕሮጀክቱ  ዶውነሮች ሲሆን የአዲሰ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ ኃላፊ አቶተክሌ በዛብህ እና የአለም አቀፍ ህፃናት አድን ድርጅት (Save the children)አመራሮች  በተገኙበት ነው።
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትሕ ቢሮ በሰው የመነገድ ሰውን በህገ ወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር ወንጀል መከላከል ማስተባበሪያ ጽ/ቤት እንደ ከተማ ወንጀሉን ለመከላከል የትብብር ጥምረቱን ተግባራት ከማስፈጸም አኳያ ያለው ድጋፍ ምን ይመስላል ፣ ከክልሎች ጋር ያለው ቅንጅታዊ ስራዎች እና የተሞክሮ ልውውጥ ፣ ያስገኘው ፋይዳዊ ለውጥ ምንደረጃ ላይ እንዳለ  ውይይት ተደርጎበታል።
የፍትህ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተክሌ በዛብህ ስራዎች ምን ደረጃላይ እንዳለ ለማየት  በመምጣታቸው አመስግነው እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት ማስተባበሪያ ጽ/ቤቱ ፕሮጀክቶችን ቀርፆ ወንጀሉን ለመከላከል እየሰራ መሆኑን ገልጸው  ስራዎቹም አበረታች እንደሆኑና በትብብር አብሮ መስራት ውጤት እንደሚያመጣ ገልጸዋል፡፡ 
ምልከታው ለቀጣይ ስራችን  አስተማሪ እና አነቃቂ የሆነ ውይይት  አድርገናል ያሉት የማስተባበሪያ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ታደሰ ፈይሳ በቀጣይም አብሮ ለመስራት የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል ብለዋል፡፡


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.