በሰው መነገድ እና ሰውን በህገወጥ መንገድ ድንበ...

image description
- ውስጥ Laws    0

በሰው መነገድ እና ሰውን በህገወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር ወንጀልን በጋራ እንከላከል ተባለ ፡፡

በሰው መነገድ እና ሰውን በህገወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር ወንጀልን በጋራ እንከላከል ተባለ ፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ቀን ታህሳስ 14/2017
ይህ የተባለው በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ በሰው መነገድ ሰውን በህገወጥ ድንበር ማሻገር ወንጀል መከላከል ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ለክ/ከተማ  ትብብር ጥምረት አባላት ከ MCDP ከተባለ ግብረ ሰናይ ድርጅት ጋር በመተባበር በ1178/2012 እና ደንብ 126/2014 የማስፈጸሚያ መመሪያዎች ላይ ስልጠና በሰጠበት ወቅት ነው፡፡
የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የጽ/ቤቱ ኃላፊ የሆኑት  አቶ ታደሰ ፈይሳ እንዳሉት በጽ/ቤቱ ህጎቹ ፣ አደረጃጀት እና መመሪያዎቹ ላይ የጋራ ግንዛቤ መያዝ ተቀራራቢ ተግባር መፈጸም  አስፈላጊና ተገቢ በመሆኑ ስልጠናው አስፈልጓል በማለት ሁሉም ባለድርሻ አካላት በክ/ከተማ ደረጃ እና ትብብር ጥምረት አባል ተቋማት የተጣለባቸውን ሀላፊነት እንዲወጡ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
ስልጠናውን የሰጡት የማስተባበሪያ ጽ/ቤት ዐቃቢ ሕግ የሆኑት አቶ ነብዩ በቀለ በአዋጅ ቁጥር 1178/2012ዓ.ም ላይ የተካተቱ የሕግ ድንጋጌዎች ምን ምን እንደሆኑና በሰው መነገድ እና ድንበር ማሻገር አዋጁን መሰረት በማድረግ በእያንዳንዱ ድርጊት ስለሚያስቀጣው የገንዘብ መጠን እና የእስራት ዘመን ከሰፊ ማብራሪያ ጋር ስልጠና ሰጥተዋል፡፡ 
በተጨማሪም ዐቃቢ ሕግ ወ/ሮ መኪያ ዲኖ  የትብብር ጥምረት መመሪያውን  መነሻ በማድረግ የትብብር ጥምረት አባላት በተለይ የስልጠናው ተሳታፊ ለሆኑ አካላት ማለትም ከሴቶች፣  ህጻናት እና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት ፣ከወጣት ና ስፖርት ጽ/ቤት እና ከፍትህ ጽ/ቤት ለመጡ ተሳታፊዎች ስላሉባቸው ሀላፊነት እና ተጠያቂነት አብራርተዋል፡፡
በመጨረሻም ከቤቱ ጥያቄዎችና ሃሳቦች ተነስተው የጽ/ቤቱ ሃላፊ ምላሽ በመስጠት ተጠናቋል፡፡


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.