ተጎጂዎች ልየታ፣ ድጋፍ እና ጉልበት ብዝበዛን በመከላከል ከዘመናዊ ባርነት ሕጻናትን ማላቀቅ በሚል ርዕስ የፖናል ውይይት ተደረገ።
ተጎጂዎች ልየታ፣ ድጋፍ እና ጉልበት ብዝበዛን በመከላከል ከዘመናዊ ባርነት ሕጻናትን ማላቀቅ በሚል ርዕስ የፖናል ውይይት ተደረገ።
።።።።።።።።።፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡።።፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡።።
የፓናል ውይይቱ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ እና ''ሆፕ ፎር ጃስቲስ'' ከተባለ ስቭል ማህበር ጋር በመተባበር የተዘጋጀ ሲሆን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትሕ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተክሌ በዛብህ ፣ የፍትህ ቢሮ አማካሪ ወይዘሮ ዘርፈሽዋል ንጉሴ፣ የሆፕ ፎር ጀስቲስ ካውንትሪ ዳይሬክተር ሶስና ይርጋ፣ ዳኞች፣ አቃቢያኔ ሕግ፣ ፖሊስ አመራር እና የማህበራዊ ዘርፍ ሙያተኞች ተሳትፈዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተክሌ በዛብህ በመክፈቻ ንግግራቸው የአለም አቀፍ ሕጻናት መብት ስምምነት ሰነድን መነሻ በማድረግ ከሕገመንግስት ጀምሮ በርካታ ዝርዝር የሕግና የፖሊስ መቃፎች መዘርጋታቸውን፣ እንደ ከተማ ለህጻናት አጠቃላይ እድገትንና መብቶቻቸውን ታርጌት ያደረጉ የህግ ማዕቀፎች አብነት ቀዳማይ ልጅነት ዙሪያ ደንብ ከ2015 ጀምሮ ስራ ላይ መዋላቸውን፣ አስተዳደሩ ከጽንስ አንስቶ ከፍተኛ ሀብት በመመደብ ባለሙያ በማስልጠንና በማሰማራት፣ በትምህርት ቤቶች ከ800ሺ በላይ ሕጻናት መመሪያ ቁሳቁስ በማሟላትና ቁርስና ምሳ በመመገብ ሀገርቱ በጸደቀቻቸው አለም አቀፍ ስምምነቶችና በወጣቻቸው ሕጎች የተገባውን ቃል በተግባር እያረጋገጠች ነው ብለዋል።
እንደ ኃላፊው ገለጻ እነዚህ በርካታ ስራዎች ቢሰሩም ቀሪ የቤት ስራዎች ሰፊ ስለሆኑ ተልዕኮ የተጣለባቸው መንግስታዊም ሆነ መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ተቀናጅቶ የችግሩ አንገብጋቢነት ዙሪያ ጋራ አረዳድ በመያዝ መረባረብ ለነጌ የሚባል እንዳይደለም አጽዕኖት ሰጥተዋል ።
በወቅቱ በፍትህ ቢሮ በሰው የመነገድ ወንጀል መከላከል ማስተባበሪያ ጽቤት ኃላፊ አቶ ታደሰ ፈይሳን ጨምሮ አምስት ፖናሊስቶች በህጻናት ፍትህ የማግኘት መብት የሕግ ማዕቀፎች፣ በህጻናት መነገድ እና ባርነት ላይ ያሉ ምርመራ ክፍተቶች፣ ለተጎጂዎች ከለላ ከመስጠት እና መልሶ ከማቋቋም፣ ህጻናት ተኮር የፍትህ ስርአት እና የህጻናት ህግ ተደራሽነት ከቅንጅታዊ አሰራር ጉደዮች በማንሳት ለፓናል ውይይት መነሻ ሃሳብ አቅርበዋል።
በፍትህ ቢሮ አማካሪ የሆኑት ወይዘሮ ዘርፈሽዋል ንጉሴ በመድረኩ ማጠቃለያ የህጻናት መብት ጥሰት በመጠኑ ይለያይ እንጂ በየቤቱ ያለ ችግር ነው በማለት ይህንን አስተሳሰብ ለመቀየር በመንግስትም በግል ተቋማትም በርካታ ስራዎች ተሰርቷል ሆኖም ከችግሩ ገና ያልተላቀቅን በመሆኑ የበለጠ የጋራ ርብርብ ሁላችንም በየዘርፋችን በማድረግ ለውጤታማነቱ እንትጋ ብለዋል።
አማካሪዋ አክለው ''ሆፕ ፎር ጃስቲስ'' ትውልድ ላይ እየሰራ ያለው ስራ የሚያስመሰግን ነው በማለት አመስግነው በቀጣይ ወንጀሉን ለመከላከል በሚያስችሉ የትኩረት አቅጣጫዎችን አቅርበዋል።
በመጨረሻም ከቤቱ የህጻናት ፍትህ ተጠቃሚነት ላይ የህግም ሆነ የአደረጃጀት ችግር እንደሌለ ተነስቶ ሁሉም የሚመለከተው አካል ተቀናጅቶ የመስራት ክፍተትን በመቅረፍ ውጤት ማምጣት አስፈላጊ እንደሆነም በማብራራት ማጠቃለያ አግኝቷል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.