የወንጀል ስነስርአት ህግን የሚመለከቱ የህገ-መን...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የወንጀል ስነስርአት ህግን የሚመለከቱ የህገ-መንግስቱ ድንጋጌዎች እና የሰብዓዊ መብት አያያዝ በሚል ስልጠና ተሰጠ፡፡

የወንጀል ስነስርአት ህግን የሚመለከቱ የህገ-መንግስቱ ድንጋጌዎች እና የሰብዓዊ መብት አያያዝ በሚል ስልጠና ተሰጠ፡፡

።።።።።።።።።

21/04/2017

ስልጠናው በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ የህግ ስርፀትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት በሁለት ዙር የተዘጋጀ ሲሆን በአዲስ አበባ ከተማ ለሚገኙ ፖሊስ ኮሚሽኖች ተሳትፈዋል።

የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የፍትህ ቢሮ የሕግ ክርክር ዘርፍ ምክትል ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ደጀኔ በአለም አቀፍ ደረጃ አንዲት ሀገር ዲሞክራሲ የሰፈነባት ናት የሚያስብላት ዋነኛው  የፍትህ ስርዓቷ ነው ብለው ለዚህም ማሳያው ፖሊስ ፣ዐቃቢህግ፣ፍርድ ቤት፣ ማረሚያ ቤት እነዚህ ተቋማት  ሰብአዊ መብት አያያዝ ስርዓታቸው ነው በማለት እነዚህ የፍትህ አካላት መመሪያ እና ደንቦችን መሰረት ያደረገ አገልግሎት በመስጠት የፍትህ ስርአቱን የማሻሻል ሂደቱን በማገዝ ሃላፊነታቸውን መወጣት ይኖርባቸዋል ብለዋል።

ኃላፊው አክለው የፖሊስ አካላት ወንጀል ሲፈፀም ምርመራ ማካሄድ ሂደት  ዲሞክራሲያዊ እንዲሆን ለማስፈፀም የሚወጡ የወንጀል ስነ ስርአት ህጎች  መሰረት በማድረግ የሰብአዊ መብት አያያዛችንን በማሻሻል ፍትህ ማስፈን ተገቢ ነው ብለዋል።

ስልጠናውን የሰጡት ዐቃቢ ሕግ ወ/ሮ ራሄል አንበርብር ሲሆኑ በአንድ ሀገር ውስጥ ጠንካራ የፍትህ ስርዓት መኖር ለኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ እድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው በመግለፅ  የኢፌዲሪ ህገ መንግስት በርካታ ድንጋጌዎች ስለፍትህና የህግ የበላይነት የሚያወሱ በርካታ ድንጋጌዎች አሉ፤ለምሳሌ በአንቀጽ 37 ስር ዜጎች ፍትህ የማግኘት መብት እንዳላቸው ተደንግጎል በማለት ስለ የወንጀል ፍትህ ፖሊሲው ዓላማና ግብ ፣ ስለ የወንጀል ሥነ ሥርዓት ፣ በሀገራችን ከወንጀል ሥነ ሥርዓት ጋር ግንኙነት ያላቸው ህጎች ፣ ህገ መንግሥቱ እና የወንጀል ሕግ ሥነ ሥርዓት  ያላቸውን ግንኙነት ፣ የወንጀል ፍትህ ፖሊሲውና የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ህገ መንግስት ፣የወንጀል ስነ-ስርዓትና የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ህገ መንግስት ሰፋ ባለ ገለፃ አቅርበዋል፡፡

የመዝጊያ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ የሕግ ስርፀት ምክር መስጠት ዘርፍ ምክትል ኃላፊ አቶ አሰፋ መብራቴ በሀገር አቀፍ ደረጃ የፍትህ ትራንስፎርሜሽን ማሻሻያ ፍኖተ ካርታ ተዘጋጅቶ በርካታ ተግባራቶች እየተከናወኑ መሆናቸውን በመግለፅ  ትኩረት ከተሰጠባቸው አንዱ ለአባላት እና ዐቃቢ ህግ እንዲሁም ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ተገቢ የሆነ የአቅም ግንባታ ስልጠና መስጠት አንዱ በመሆኑ አመኔታ ሊኖረው የሚችል ተቋም መገንባት ጥረት ውስጥ የእናንተ ሚና ትልቅ አስተዋፅኦ አለው በማለት የፍትሕ ስርዐት ፖሊሲው ላይ በርካታ ጉዳዮች አሉ፤ ትኩረት ተሰጥቶባቸው ከሚሰሩት አንዱ የሰብአዊ መብት አያያዝ ነው ብለው የዜጎች መብት እንዲከበር ፣ የሰብአዊ መብት ጥሰት እንዳይኖር ፣ ወንጀልን በመከላከል ረገድ ከፍርድ ቤት፣ከዐቃቢ ህግ ፣ከማረሚያ ቤቶች እና ከፖሊስ ጋር በጋራ በመሆን  ስራን ማሳለጥ ይኖርብናል በማለት ገልፀዋል፡፡

በመጨረሻም ከቤቱ ሃሳብ አስተያየት በመስጠት ዐቃቢ ሕጓ ምላሽ በመስጠት ስልጠናው ተጠናቋል፡፡


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.