የ6 ወራት የመንግስት እና የፖርቲ ስራዎች አፈፃ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የ6 ወራት የመንግስት እና የፖርቲ ስራዎች አፈፃፀም ምልከታ ተደረገ ።

የ6 ወራት የመንግስት እና የፖርቲ ስራዎች አፈፃፀም ምልከታ ተደረገ ።

።።።።።።።።።።

በከንቲባ ጽ/ቤት የከንቲባ አማካሪ በሆኑት በአቶ ጥላሁን ከበደ የሚመራ 6 ኮሚቴ በተገኙበት ምልከታ ተካሂዷል።

በስድስት ወራት ውስጥ ቢሮው ከተገበራቸው የክርክር ስራዎች፣ ከሰብአዊ መብት አያያዝ፣ ከንቃተ ህግ ህግን ተደራሽ ከማድረግ፣

በሀብት አጠቃቀም ፣በተቋም ግንባታ ምቹ ሁኔታ ከመፍጠር ፣አገልግሎት አሰጣጥ፣ ከሌብነት እና ብልሹ አሰራርን ተጠያቂነት ከማስፈን፣መልካም አስተዳደር ችግሮችን ከመፍታት፣ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት ከመስራት፣ ሪፎርሙ ያለበትን ደረጃ እና የኢንሼቲቭ ስራዎችን የአካል ምልከታ ተደርጓል።

በወቅቱ በአዲስ አበባ ከተማ ፍትህ ቢሮ የቢሮው ኃላፊውን አቶ ተክሌ በዛብህን ጨምሮ በየደረጃው ያሉ አመራሮች ከኮሚቴው ለቀረበ ጥያቄ በመረጃ የተደገፈ ምላሽ ሰጥተዋል።

በማጠቃለያ መርሃግብሩ በከንቲባ ጽ/ቤት የከንቲባ አማካሪ በሆኑት በአቶ ጥላሁን ከበደ  ፍትህ ቢሮ ባለፈው አመት ተሸላሚ ተቋም መሆኑን ገልጸው ያንን አስጠብቆ ለመሄድ እየሰራ እንደሆነ ተመልክተናል ብለው በተለይ የህዝብን ለማስጠበቅ በትጋት እየተሰራ መሆኑን እቅድዶችን እና ሪፖርቶች ሂደቱን በጠበቀ መልኩ መሰራቱ፣ ምቹ የስራ ሁኔታ እተየፈጠረ ያለበት መንገድ ለሌላው አስተማሪ እንደሆነ ባጠቃላይ የመንግስትን እና የፖርቲ ስራዎች በጥሩ ሁኔታ እየተመራ እንደሆነ አይተናል ብለዋል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.