እጩ አቃቢያነ ህግ ቃለመሀላ ፈጸሙ።
እጩ አቃቢያነ ህግ ቃለመሀላ ፈጸሙ።
።።።።።።።
ታህሳስ 24/2017
ቃለ መሀላውን የፈፀሙት በቢሯችን በቅርቡ በዕጩ አቃቤ ህግነት ተወዳድረው ያለፋ የህግ ምሩቃን ናቸው።
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ የሕግ ክርክር ዘርፍ ምክትል የቢሮ ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ደጀኔ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ባስተላለፉበት ወቅት እንደ ሃገር የተጀመረውን የፍትህ ትራንስፎርሜሽን ቢሮአችንም ወደ ተግባር ገብቶ መጠነ ሰፊ ስራዎች እየሰራ ይገኛል ብለው ከስራዎቹ መካከል ብቁ ፣ በስነምግባር የታነጸ እና በክህሎት የዳበረ ዐቃቢ ህግ ማፍራት በመሆኑ ዛሬ ቃለ መሃላ የፈጸማችሁ አቃቢያነ ህግ ይህንን በመገንዘብ ባላችሁ እውቀት በተጨማሪ በየእለቱ በማንበብና ከነባር ባለሙያዎች ልምድ በመቅሰም ራሳችሁን በማብቃት ተወዳዳሪ በመሆን በቅንነት በመስራት የህብረተሰባችንን የፍትህ ፍላጎት በማርካት የተጀመረውን ለውጥ ማገዝ ከናንተ ይጠበቃል በማለት አሳስበዋል።
በፍትህ ቢሮ የጉባኤ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አብይ አስናቀ እጩ አቃቤያነ ህጉን የተቋሙ አመራሮች በተገኙበት ቃለ-መሃላ አስፈጽሟል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.