ፍልሰተኞችን የተመለከተ አለማቀፋዊ እና ሀገራዊ...

image description
- ውስጥ Laws    0

ፍልሰተኞችን የተመለከተ አለማቀፋዊ እና ሀገራዊ ህጎች አተገባበር ዙሪያ ውይይት ተደረገ።

ፍልሰተኞችን የተመለከተ አለማቀፋዊ እና ሀገራዊ ህጎች አተገባበር ዙሪያ ውይይት ተደረገ።

:::::::::::::::::::::::::::::::::::

የአዲስአበባ  ከተማ አስተዳደር ፍትሕቢሮ በሰው መነገድ ሰውን በህገወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር ወንጀል ላይ ያሉ አለማቀፋዊ እና ሀገራዊ ሕጎች አተገባበር ላይ ለዐቃቢሕግ ፣ ለፖሊስ እና ከየክፍለ ከተማ ስራና ክህሎት ጽ/ቤት እንዲሁም ትምህርት ጽ/ቤቶች ከአለም አቀፍ ህጻናት አድን ድርጅት ጋር በመተባበር ስልጠናውን ተጥተዋል::

የፍትህ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተክሌ በዛብህ በመክፈቻ ንግግራቸው ወንጀሉን ለመግታት በርካታ ስራዎች የተሰሩ ቢሆንም አሁንም በስፋት ያለ በመሆኑ በልዩ እቅድና ተቋማዊ አቅም በመገንባት መንቀሳቀስ እንደሚገባ አመላክቷል።

በተለያዩ ጊዜያት ኢትዮጲያ ያጸደቀቻቸው ስምምነቶች ፕሮቶኮሎች እንዲሁም በአዋጅች ፣በደንብ እና መመሪያዎችን  በተመለከተ ሰፋ ያለ ገለጻ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.