ቢሮው የ6 ወር የቅንጅት ስራዎች እቅድ አፈጻጸም...

image description
- ውስጥ Laws    0

ቢሮው የ6 ወር የቅንጅት ስራዎች እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት  ላይ የባለድርሻ አካላት ተቋማት፣ የክፍለ ከተማ የፍትህ ጽ/ቤት ኃላፊዎች  እና የሲቭክ ማህበራት በተገኙበት ውይይት  አካሂዷል።

''የፍትህ ስሮዓቱን ለማሻሻል በሚደረግ ሂደት የባለድርሻ አካላት  ሚና ከፍተኛ ነው''

 

አቶ ተስፋዬ ደጀኔ

የአዲስ አበባ ከተማ ፍትህ ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ

 

ጥር/20 ቀን 2017 ዓ.ም

 

ቢሮው የ6 ወር የቅንጅት ስራዎች እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት  ላይ የባለድርሻ አካላት ተቋማት፣ የክፍለ ከተማ የፍትህ ጽ/ቤት ኃላፊዎች  እና የሲቭክ ማህበራት በተገኙበት ውይይት  አካሂዷል።

 

ባለፉት ስድስት ወራት ቢሮው ከባለድርሻ  ተቋማት ጋር  በቅንጅት በመስራት የፍትህ ስርዓቱን በማሻሻል ሂደት ላይ አቅም በመሆን ወጤት መምጣቱን የገለጹት

የፍትህ ቢሮ ምክትል  ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ደጀኔ ናቸው።

 

የከተማ አስተዳደሩን እና የነዋሪውን መብት እና ጥቅም ማስጠበቅ ብሎም በህግ የተሰጠንን ስልጣን ወቅቱ በሚጠይቀው ልክ ለመወጣት የባለድርሻ አካላት ሚና ከፍተኛ በመሆኑ በስራ ሂደት ወቅት የሚነሱ ችግሮችን በመቅረፍ  ተገቢውን  ድጋፍ ማድረግ   እንዳለባቸው አቶ ተስፋዬ ደጀኔ ገልጸዋል።

 

ምክትል ኃላፊው አክለውም በተለይ ተቋማትን ወክለን ፍርድቤት ቆመን በምናደርጋቸው ክርክሮች ላይ በህግ ጉዳዮች በፍታብሔራዊ ክርክር 93.2% በመርታት የአስተዳደሩን የ1.7 ቢሊዮን ብር የሚገመት ሀብት በማዳን ጉዳት እንዳያስከትል በማስወሰን አስከብረናል።

ከወንጀል ጉዳዮች ጋር በተያያዘ የምርመራ መዝገቦችን በማጥራት በተለይ በግል አቤቱታ ከቀረቡ ወንጀሎች ከ5ሺ በላይ መዝገቦች በእርቅ እንዲጨርሱ በማድረግ ዜጎች ከፍርድ ቤት ምልልስ በማህበራዊ ጉዳያቸው እንዲያሳልፉ ዕድል ይፈጥራል በአጠቃላይ የወንጀል የመርታት አቅም 99% ማሳካት መቻሉ የሚበረታታ ነው ።

 

በወቅቱ አግባብ ያለውን መረጃ የሚልኩ እንዳሉ ሁሉ መረጃዎችን ሲጠየቁ ማዘግየት፣አስጠቂ የሆኑ መረጃዎችን መላክ፣ትክክለኛ ምስክሮችን ያለማቅረብ እኝህ በአሉታ የተነሱት ላይ በአጭር መድረኮች እየፈታን በቀጣይ ቅንጅታዊ ስራችንን ለጋራ ውጤታማነት እንሰራለን፣በተጨማሪም ስለ ህጎች ተደራሽነት የህግ ረቂቅ ውሎች በፍትሕ ቢሮ በግምገማ እንዲያልፍ በማድረግ ከተማችን የተለያዩ የህግ ማዕቀፎች እንዲኖራት ተቋማት በስራ ላይ እንዲያውሉ  በማረጋገጥ በጋራ ለመስራት መተባበር ያስፈልጋል ብለዋል።

 

በመጨረሻም አቶ ሙሉነህ ደሳለኝ የሰላም ፍትህና መልካም አስተዳደ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ እና በፍትህ ቢሮ ምክትል ኃላፊዎች አቶ ተስፋዬ ደጀኔ እና አቶ አሰፋ መብራቴ ለተነሱ ሃሳብ እና ጥያቄዎች ምላሽ በመስጠት በቀጣይ ስድስት ወራት  ባለድርሻ አካላት ያለፍትህ ልማት ፣ እድገት እንደማይኖር በመገንዘብ የቅንጅት ስራውን በማጠናከር የተጀመረውን ለውጥ በማገዝ ከግብ ማድረስ ከሁሉም ይጠበቃል ብለዋል።

 

ቢሮው  በበጀት አመቱ መጀመሪያ ከባለድርሻ  አካላት ጋር በቅንጅት ለመስራት የስምምነት ሰነድ መፈራረሙ ይታወሳል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.