
በደንብ መተላለፍና ክስ አቀራረብ ዙርያ ግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መሰጠት ተጀመረ፡፡
በደንብ መተላለፍና ክስ አቀራረብ ዙርያ ግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መሰጠት ተጀመረ፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
የካቲት 01/2017
በክ/ከተማ እና በማዕከል ደረጃ ያሉ የህግ ክርክር ዘርፍ ዳይሬክተሮች እና ዐቃብያነ ህግ በተገኙበት በደንብ ቁጥር 167/2016 በማህበራዊ ፍርድ ቤት በደንብ መተላለፍና ክስ አቀራረብ ዙሪያ ግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መሰጠት ጀምሯል፡፡
መርሃ ግብሩን ያስጀመሩት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ የህግ ጉዳዮች ክርክር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክትር አቶ ናሆም ሰለሞን በደንብ ቁጥር 167/2016 ከተሻሻለ በኋላ የከተማ አስተዳደሩ የከተማውን ውበት ከማስጠበቅ ባሻገር ህግ አክባሪ ማህብረተረሰብ ለመፍጠር እያደረገ ባለው ዘርፈ ብዙ እንቅስቃሴ ዉስጥ ደንብ 167/2016 ማስፈጸም አይነተኛ ሚና ከሚጫወተው አንዱ ከቅጣቱ የሚገኘው ገቢ ከፍተኛ መሆኑን ገልጸው ለአብነት በ2017 ግማሽ አመት ከደንብ ማስፈጸም ብቻ እንደ ፍትህ ቢሮ 2.2 ሚሊየን ገቢ ለከተማ አስተዳደሩ መሰብሰቡን ገልጸዋል፡፡
ዳይሬክተሩ አክለውም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳር ፍትህ ቢሮ በአዋጅ በተሰጠው ስልጣን መሰረት የህግ የበላይነትን የማስጠበቅ ተልዕኮ ለመወጣት ደንቡ ጉልህ ድርሻ አለው ብለዋል፡፡
ቢሮው በየጊዜ እያስመዘገበ ባለው ጥሩ አፈጻጸም የሚያበረታታ ቢሆንም በክርክርዳይሬክቶሬት በደንብ 167/2016 ከአምናው አፈጻጸም አንጻር መሻሻል ያለ ስለመሆኑ በግምገማችን የታየ ሲሆን ከእቅዳችን አንጻር ግን ስራ እደሚጠበቅብ እና ስራዉን በተሳካ ሁኔታ ለመወጣት በተቋማችን ያሉ አቃብያነ ህጎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በመውሰድ በዘርፉ ያለውን ጉድለት ማሻሻል እንደሚያስፈልግ ታምኖ ስልጠናውን ለመስጠት አስፈልጓል ብለዋል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ የህግ ጥናት ምርምር እና ማርቀቅ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጀማል ሳላህ ደንብ ቁጥር 167/2016 አስመልክተው ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
ስልጠናው በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ የህግ ስርጸትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት የተዘጋጀ መሆኑንና በተለያየ ዙር ለሁሉም አቃብያነ ህግ እንደሚሰጥ ለማወቅ ተችሏል፡፡
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.