
በፕሮጀክት አፈፃፀም ዙርያ ውይይት ተደረገ ፡፡
በፕሮጀክት አፈፃፀም ዙርያ ውይይት ተደረገ ፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
03/06/2017
ውይይት የተደረገው ከአየርላንድ ከመጡ የፕሮጀክቱ ፋይናንስ ደጋፊዎች ሲሆን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተክሌ በዛብህ ፣ Rory Sturdy, Media, APA (CVM partner in Ireland) እ ና የCVM ማህበራዊ ፕሮግራም ኃላፊ የሆኑት ወ/ሮ ፀሃይ ሞገስ በተገኙበት ነው።
የፍትህ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተክሌ በዛብህ ስራዎች ምን ደረጃ ላይ እንዳለ ለማየት በመምጣታቸው አመስግነው እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት ማስተባበሪያ ጽ/ቤቱ ፕሮጀክቶችን ቀርፆ ወንጀሉን ለመከላከል እየሰራ መሆኑን በመግለጽ ስራዎቹም አበረታች እንደሆኑና በትብብር አብሮ መስራት ውጤት እንደሚያመጣ ገልጸዋል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትሕ ቢሮ በሰው የመነገድ ሰውን በህገ ወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር ወንጀል መከላከል ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ ዮሀንስ ብርሃኑ እንደ ከተማ ወንጀል መከላከልና ህግ ማስከበር ፣ ተጎጂዎችን መልሶ በማቋቋም ፣ ለወንጀሉ ሰለባዎቹ አስፈላጊውን ጥበቃ እንድኖር እንዲሁም የተለያዩ ባለድርሻ አካላትን በትብብር ጥምረት ሥር ያሉትን በማጠናከር ዉጤታማ ሆነናል ብለዋል ።
የጽ/ቤት ኃላፊው አክለውም በሰው የመነገድ ወንጀል ለመከላከል በአንድ ተቋም ብቻ በመስራት ውጤታማ መሆን ስለማይቻል መሰል ግብረ ሰናይ ድርጅቶች ጋር መስራት ያስፈልጋል በማለት CVM ግብረ ሰናይ ድርጅት በርካታ ስራዎችን አብሮ በመስራት ውጤታማ ሆነናል በቀጣይም ተግባራቶችን በጋራ አሰራር በመዘርጋት መስራት እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል፡፡
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.