በቢሮው የሕግ ክርክር ዘርፍ በ2017 በጀት ዓመ...

image description
- ውስጥ Laws    0

በቢሮው የሕግ ክርክር ዘርፍ በ2017 በጀት ዓመት የ7 ወር አፈፃፀም ሪፖርት ገመገመ፡፡

በቢሮው የሕግ ክርክር ዘርፍ በ2017 በጀት ዓመት የ7 ወር አፈፃፀም ሪፖርት ገመገመ፡፡ 

።።።።።።።

አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ የህግ ጉዳዮች ክርክር ዘርፍ የ7 ወራት  አፈጻጸሙን ከክ/ከተማ የክርክር እና የወንጀል ዳይሬክተሮች በተገኙበት  ተገምግሟል።

ግምገማውን የፍትህ ቢሮ ምክትል ሃላፊ የህግ ክርክር ዘርፍ ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ደጀኔ መርተውታል።

በወቅቱ በዘርፉ ታቅደው እየተከናወኑ ካሉ ተግባራት ውስጥ የመንግስትን እና የህዝብን ጥቅም ከማስጠበቅ ረገድ ህገወጥ የመሬት ወረራን ፣ የመንግስት ቤቶችን ፣የልማት ፕሮጀክቶችን፣ሼዶችን አስመልክቶ የሚደረጉ ክርክሮች እንዴት እየተመሩ እ እንደሚገኙ እና ስራዎች በቴክኖሎጂ መደገፋቸውን ፣የማረፊያ ቤት ክትትልን አስመልክቶ በተለይ ደግሞ የዓቃቢያነ ህግ ስነምግባር አንጻር በዝርዝር ተገምግሟል።

በወቅቱ የማዕከል እና ከየክፍለ ከተሞች የመጡ የፍታብሔር ዳይሬክተሮች እና ወንጀል ዳይሬክተሮች አጠቃላይ የ7ወራት አፈፃፀማቸውን ከአበይት ተግባራት አንፃር በነበረ ጠንካራ እና ደካማ ጎን እንዲሁም በቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ አንፃር አቅርበዋል።

አቶ ተስፋዬ ደጀኔ በማጠቃለያቸው የ7ወራት የመፈጸም አቅማችን 94% መሆኑ የሚያበረታታ ነው ብለው  ለቀጣይ   ትኩረት  ያሉት በተለይ፦ ዉጤታማ  ክርክር ማድረግ ይገባል ያሉት የመንግስት የልማት ፕሮጀክቶች ፣  የመሬት ወረራ እና ህገወጥ ግንባታዎች እንዲሁም የመንግት ቤቶች አስመልክተው የሚደረገው የፍ/ቤት ክርክሮች ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት መመራት ያለባቸው መሆኑን አሳስበዋል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.