“ከቃል እስከ ባህል“ በሚል መርህ ቃል  የሲቪል...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

“ከቃል እስከ ባህል“ በሚል መርህ ቃል  የሲቪል ሰርቪስ ሠራተኞች በመንግስት የቀጣይአቅጣጫዎች ዙሪያ ውይይት ተደረገ፡፡

“ከቃል እስከ ባህል“ 

“ከቃል እስከ ባህል“ በሚል መርህ ቃል  የሲቪል ሰርቪስ ሠራተኞች በመንግስት የቀጣይአቅጣጫዎች ዙሪያ ውይይት ተደረገ፡፡

06/06/2017

በውይይቱ የአዲስ አበባ ፍትህ ቢሮ እና ታክስ ይግባኝ ኮሚሽን አመራር እና ሰራተኞች ተሳትፈዋል።

ጠንካራ ጠንካራ ተቋም መገንባት፣ ብሄራዊ ገዥ ትርክትን ማጠናከር ፣ የፍህ ዘርፍ ትራንስፎርሜሽን ከመምራት ኢኮኖሚ እና ልማትን ከማፋጠን፣ ማህበራዊ ብልጽግና ከማረጋገጥ ውጤታማ የዲፕሎማሲ ስራዎችን ከማጠናከር አንጻር ውይይት ተካሄዷል።

የመወያያ ሰነድ ያቀረቡት የታክስ ይግባኝ ኮሚሽን ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ በሀይሉ ክብረት ሲሆኑ በሰነዱ የቀረቡ አስር ነጥቦችን በዝርዝር ባብራሩበት ወቅት ሲቪል ሰርቫንቱ ከዚህ አንጻር ተረድቶና ተገንዝቦ ድርሻውን አውቆ ርብርብ እንዲያደርግ መንግስት የውይይት መድረክ አዘጋጅቷል ብለዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ግርማ ወርቁ አንድ ሀገር አደገች የምንለው  በሰላም፣ በኢኮኖሚ ፣ በማህበራዊ እና በዲፕሎማሲው ረገድ በምታሳየው ለውጥ ሲሆን ለዚህ ደግሞ ህዝቦች በትብብር እና በቅንጅት በመስራት ሲሆን  እኛ እንደ ሀገር ካለን ታሪክ በአንድም በሌላ የተሳሰርን የተጋመድን በመሆናችን እሴታችንን ጠብቀን ከሰራን መንግስት ያስቀመጠውን የትኩረት አቅጣጫ ከግብ ማድረስ እንችላለን በማለት ሁሉም የመንግስት ሰራተኛ የሚጠበቅበትን በሃላፊነት መወጣት ይኖርበታል ብለዋል።

የታክስ ይግባኝ ኮሚሽን ፕሬዝዳንት አቶ ታረቀኝ አስፋው  እንዳሉት አቅጣጫው ከእስትራቴጂክ እቅድ የተቀዳ ሲሆን ነገር ግን ትኩረት ሊሰጠው ያስፈለገው በሶስት አመት ውስጥ 8.4% እድገት ለማምጣት በሚያስችል መልኩ በተለይ ደግሞ ሀገሪቷያለባትን እዳ በ3% እየቀነሱ ለመሄድ እንዲያስችል ታቅዶ ነው በማለት ገልጸዋል፡፡

የውይይቱ ተሳታፊዎች ማህበራዊ ጉዳዮችን የሚዳስሱ ሰነዶች ለውይይት  መቅረቡ የሚያበረታታ ስራ ነው ተጠናክሮ ይቀጥል በማለት እየተሰራ ያለው ሰው ተኮር የልማት ስራ ሃገር የሚያኮራ ነው በማለት መንግስት በኑሮ ውድነት ሁኔታና በሰላም ዙርያ የሚሰራውን ስራ አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ጠይቀዋል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.