በደንብ መተላለፍና ክስ አቀራረብ ዙርያ ሲሰጥ የ...

image description
- ውስጥ Laws    0

በደንብ መተላለፍና ክስ አቀራረብ ዙርያ ሲሰጥ የነበረው ግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተጠናቀቀ፡፡

በደንብ መተላለፍና ክስ አቀራረብ ዙርያ ሲሰጥ የነበረው ግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተጠናቀቀ፡፡

፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡

የካቲት 15/2017

በክ/ከተማ እና በማዕከል ደረጃ ያሉ የህግ ክርክር ዘርፍ   ዳይሬክተሮች እና ዐቃብያነ ህግ  በተገኙበት በደንብ ቁጥር 167/2016 በማህበራዊ ፍርድ ቤት በደንብ መተላለፍና ክስ አቀራረብ ዙሪያ ሲሰጥ የነበረውን  ግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተጠናቋል፡፡

የመዝጊያ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ የሕግ ስርፀት ምክር መስጠት ዘርፍ ምክትል ኃላፊ አቶ አሰፋ መብራቴ እንዳሉት ከተማ አስተዳደሩ በከፍተኛ ፍጥነት በለውጥ ሂደት ውስጥ ይገኛል በማለት ተቋማችን በዚሁ ልክ  እያደገና እየደረጀ በመሆኑ  በሁሉም ዘርፍ የስራ ባህልና አስተሳሰብ በመለወጥ የጀመርነውን ትጋት በበለጠ በማስቀጠል ከቀደመው ይልቅ አሁን የበለጠ መትጋት መስራት ይጠበቃል ብለዋል፡፡

ስልጠናውን የሰጡት  በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ የህግ ጥናት ምርምር እና ማርቀቅ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጀማል ሳላህ  በደንብ መተላፍ ክስ አቀራረብ  ደንብ ቁጥር 167/2016 እና የወንጀል ህግ  አስመልክተው ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ስልጠናው በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ የህግ ስርጸትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት የተዘጋጀ ሲሆን  በተለያየ ዙር ለሁሉም አቃብያነ ህግ እንደተሰጠ ታውቋል ፡፡


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.