
አገልግሎት መስጫ ተቋማትን በማደስ አገልግሎት አሰጣጡን ማዘመን ያስፈልጋል።
አገልግሎት መስጫ ተቋማትን በማደስ አገልግሎት አሰጣጡን ማዘመን ያስፈልጋል።
።።።።።።።።።።።።።
ከተማ አስተዳደሩ በአገልግሎት ዘርፈ በበቃ የሰው ሀይል ልማት፣ በቴክኖሎጂ እና በሕግና አሰራር ስማርት ከተማ ለመገንባት ሰፊ ጥረት እያደረገ ባለበት በዚህ ወቅት ተቋማትም ይህንን በመተግበር ሂደቱን ማገዝ ይጠበቃል አቶ ተክሌ በዛብህ የፍትህ ቢሮ ኃላፊ።
ይህንን ያሉት የአዲስአበባ ከተማ ፍትህ ቢሮ የመሰብሰቢያ አዳራሽ እና ሌሎች የአገልግሎት መስጫዎች ታድሰው ለአገልግሎት ክፍት ባደረጉበት ወቅት ነው።
ኃላፊው አክለውም የከተማችን ተቋማትን ስማርት የማድረግ እቅድ ለማሳካት እንደ ቢሮአችን ለሰራተኛው ምቹ የስራ አካባቢ ከመፍጠር አንጻር የሰራተኛ ካፍቴሪያ፣ የህጻናት ማቆያ ፣ ዛሬ ታድሶ ለአገልግሎት ክፍት የተደረገው የመሰብሰቢያ አዳራሽ ጨምሮ የሚጠቀሱ ናቸው ብለዋል።
ኃላፊው በንግግራቸው አገልግሎት መስጫዎችን ማደስ ብቻ ሳይሆን
አገልግሎት አሰጣጡንም በማደስ ወቅቱን የዋጀ አገልግሎት መስጠት ያስፈልጋልም ብለዋል።
በእለቱ በህንጻው ላይ አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማት አመራሮችና ሰራተኞች በተጀመሩ አገልግሎቶች የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.