
ፌዴራል ሕግና ፍትህ ኢንስቲትዩት ከፍትህ ቢሮ በመተጋገዝ ለ200 በላይ ዐቃቢያነህግ ስልጠና መስጠት ጀመረ።
ፌዴራል ሕግና ፍትህ ኢንስቲትዩት ከፍትህ ቢሮ በመተጋገዝ ለ200 በላይ ዐቃቢያነህግ ስልጠና መስጠት ጀመረ።
።።።።።።።።።። ።።።።።።።።
ማስጀመሪያ መርሐ ግብሩ ላይ የፌደራል ህግና ፍትሕ ኢንስቲትዩት በሚንስትር ድኤታ ማዕረግ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ዘካሪያስ ኤርኮላ ፣የአዲስ አበባ ፍትህ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተክሌ በዛብህ ጨምሮ ሌሎች በየደረጃው ያሉ አመራሮች ተገኝተዋል።
የፌደራል ህግና ፍትሕ ኢንስቲትዩት በሚንስትር ድኤታ ማዕረግ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ዘካሪያስ ኤርኮላ በማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ አዲስ አበባ እንደስሟ አዲስ ጽዱ ከተማ እየሆነች ባለችበት በዚህ ወቅት ዐቃቢያነ ሕግ ንጹሕ የሆነ አገልግሎት እንዲሰጥ ይጠበቃል ብለው ተቋማችን እንደ ሀገር አንዱ እንደ ክፍተት ሲነሳ የነበረውን የህግ ሙያ ማሰልጠኛ ማዕከል በበቂ አለመኖር ሲሆን በሌለባቸው አከባቢዎች ተደራሽነትን በማስፋት የፍትህ አካላት የማብቃት ስራ እየሰራን እንገኛለን ብለው ተቋማት ይህንን እድል በተገቢው በመጠቀም በፍትህ ስርዐት የሚታዩ ክፍተቶችን ማሟላት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።
የአዲስ አበባ ፍትህ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተክሌ በዛብህ በበኩላቸው የፌደራል ሕግና የፍትህ ኢንስቲትዩት የፍትህ ስርዓቱን ለማሻሻል የተሰጠን ተልዕኮ ለማሳካት እያደረገ ያለው ዘርፈ ብዙ ተግባር የሚያበረታታ ነው ብለው ተቋማችን ለማገዝ እየሰራ ያለውን ስራ እጅግ የሚያስመሰግን ነው በማለት ለተቋሙ ምስጋና አቅርቧል።
አቶ ተክሌ አክለውም ተቋማችን ከተማዋ እያካሔደች ካለችው ዘርፈ ብዙ ሪፎርም እንዲሁም በሀገር ደረጃ እየተካሔደ ካለው የፍትህ ዘርፍ ትራንስፎርሜሽን ጋር ተጣጣሞ እንዲሔድ ስራዎች እየተሰራ ይገኛል በማለት አንዱ የዓቃቢያነ ሕጉን አቅም መገንባት ነው ብለው ስልጠናው ወሳኝ እና በግምገማ የተለዩ የተመረጡ ርዕሰ ጉዳዮች በመሆናቸው ሰልጣኞች በልዩ ትኩረት በመከታተል ወደ ተግባር መለወጥ ይኖርባቸዋል ብለዋል።
ስልጠናው በኮንስትራክሽንህግ ፣ በወንጀል ስነ-ስርዓት፡- (ክስ አመሰራረትና የክስ ሂደት አመራር ፣ የፍታሐብሄርስነ-ስርዓት ህግ (አቤቱታ አዘገጃጀት፣የክርክር አመራር፤ የይግባኝና የሰበር አቤቱታ ፣ ለህዝብጥቅም ሲባል ስለሚለቀቅ ንብረት (law of expropriation for public use ፣በመሬት ይዞታ ላይ የሚነሱ ክርክሮች አድማስ ላይ ለ5 ዙር የሚሰጥ መሆኑን የፍትህ ቢሮ ዐቃ ቢያነሕግ ጉባኤ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አብዮት ጂፋራ አሳውቀዋል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.