በሰው መነገድና በሕገ-ወጥ መንገድ ድንበር የመሻ...

image description
- ውስጥ Laws    0

በሰው መነገድና በሕገ-ወጥ መንገድ ድንበር የመሻገር ወንጀልን መከላከል  የሁሉም አካላት ጉዳይ መሆን አለበት።

በሰው መነገድና በሕገ-ወጥ መንገድ ድንበር የመሻገር ወንጀልን መከላከል  የሁሉም አካላት ጉዳይ መሆን አለበት።

።።።።።።።።።   ።።።።።።።።።

መጋቢት 20/2017 ዓ.ም

አዲስ አበባ ፍትህ ቢሮ

 

ይህ የተባለው በፍትህ ቢሮ በሰው የመነገድ እና ድንበር የማሻገር ወንጀል ተከላካይ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት" በህጋዊነት ድንበር መሻገርንና ስራ ስምሪትን እናበረታታለን" በሚል መሪ ሃሳብ የክፍሉን የ7ወር እቅድ አፈጻጸም በተገመገመበት ወቅት ነው።

በወቅቱ የአዲስ አበባ ከተማ  ፍትህ ቢሮ በየደረጃው ያሉ አመራሮች፣ የማስተባበሪያ ጽ/ቤቱ የትብብር ጥምረት ተጠሪ አባላት እና cvm ግብረ ሰናይ ድርጅት አመራር እና ባለሞያዎች ተገኝተዋል።

የፍትህ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተክሌ በዛብህ በመልዕክታቸው  ኢትዮጵያ ካላት ክብርና ኩራት አንጻር ከህገውጥ ፍልሰት በእጅጉ የማይጣጣም ከመሆኑም የሰው ሕይወትና የሀገር ደህንነት ስጋት በመሆኑ የምንግዜም አጀንዳ መሆን አለበት ብለዋል።

ኃላፊው አክለው በሰው የመነገድ ወንጀልን ለመከላከል ከከተማ እስከ ታችኛው እርከን ድረስ አደረጃጀቶችን በማዋቀር  ምክር ቤት በመመስረት ስራዎችን እየሰራን እንገኛለን ብለዋል።

አቶ ተክሌ የከተማችን ወጣቶች በሀገር ውስጥ የሚፈጠሩ ስራዎች ሳያማርጡ በመስራት ይህ ባልሆነ ግዘ ሁሉ በሕጋዊነት በውጪ ሀገራት መንግስት በሚያመቻቻቸው ስራዎች መሰማራት እንጂ በሕገ ወጥ ደላላዎች እንዳይደለሉ በራሳቸው ስራ ለመፍጠር ጭምር የሚበቃውን ገንዘብ እንዳይባክኑ አሳስቧል።

የትብብር ጥምረቱ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዮሃንስ ብርሃኑ በበኩላቸው የሰውን ህይወት ማዳን የሁሉም አካላት ጉዳይ መሆን አለበት በማለት የ7ወራት አፈጻጸሙ የሚያጠነጥነው ያሉት ወንጀሉን በመከላከል ፣ በመቆጣጠር ፣ተጎጂዎችን ለማቋቋም እንዲሁም በቅንጅት የተሰሩ ስራዎችን ያገናዘበ ነው ብለዋል ።

የማስተባበሪያ ጽ/ቤቱን የ7ወራት አፈጻጸም ሪፖርት ያቀረቡት ዓቃቢ ህግ ሚስጢረ አፈወርቅ ሲሆኑ በስራ ቡድኖችና በክፍለከተማ ደረጃ የተተገበሩ ስራዎችን ከሰፊ ማብራሪያ ጋር አቅርበዋል።

የፍትህ ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ደጀኔ በበኩላቸው አዲስ አበባ የወንጀሉ መነሻ፣ መተላለፊያ እና መዳረሻ በመሆኗ ህገወጥ ፍልሰትን ለመከላከል ወቅቱን የዋጀ እቅድ፣ ትግበራ፣ ክትትልና ቁጥጥር በማድረግ ውጤት ላይ ያነጻጸረ ስራ ከሁሉም ባለድርሻ አካላት ይጠበቃል ብለዋል።

በመጨረሻም የትብብር ጥምረት ጽ/ቤቱ የተመደቡ  አዲስ ኃላፊ አቶ ዮሃንስ ብርሃኑ ጽ/ቤቱን ሲያስተባብር ከነበሩት ከአቶ ታደሰ ፈይሳ የስራ ርክክብ የተደረገ ሲሆን

ቢሮው ለአቶ ታደሰ ፈይሳ የምስጋናና እውቅና ምስክር በመስጠት ተጠናቋል።

📞 በሰው የመነገድ፣ ሰውን በሕገወጥ ድንበር የማሻገር እና ሕገወጥ ስራ ስምሪት ጋር በተገናኘ ጥቆማ ለመስጠት ሆነ ምክር ለማግኘት ዘወትር በስራ ሰዓት በነጻ የስልክ መስመራችን 6073 ይደውሉልን።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.