
በሰብአዊ መብት አያያዝ ዙርያ ስልጠና ተሰጠ፡፡
በሰብአዊ መብት አያያዝ ዙርያ ስልጠና ተሰጠ፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
21/06/2017
ስልጠናው የተሰጠው በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ የሕግ ስርጸትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት እና ሰብአዊ መብት ድርጊት መርሃ ግብር ጋር ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ጋር በመተባበር በከተማ አስተዳደሩ ለሚገኙ ፖሊስ አባላት በሰብአዊ መብት አያያዝ ዙርያ ስልጠናው ተሰጥቷል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ ምክትል ሃላፊ አቶ አሰፋ መብራቴ በመክፈቻ ንግግራቸው በሕገ-መንግስታችን ሰብአዊ መብትን አስመልክቶ ሰፊ ማብራሪያ የተሰጠው ለሃገር መረጋጋት እና ለሰላም መስፈን ትልቅ ሚና ስላለው ነው ብለዋል።
ኃላፊው አክለው የፍትህ ትራንስፎርሜሽን ትግበራ አንዱ የፍትህ አገልግሎት አሰጣጡን ማሻሻል በመሆኑ የፍትህ አካላትን የአቅም ግንባታ ስራ መስራት ነው በማለት ፖሊስና ሰብአዊ መብት ደግሞ የተቆራኘ ተግባር ስላላችሁ የፍትህ ስርአቱን ለማሻሻል ያስችላል ብለው ሰልጣኞች ስልጠናውን በአግባቡ በመከታተል ውጤታማ ለማድረግ የሚጠበቅባችሁን ሃላፊነት እንድትወጡ በማለት አሳስበዋል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ የሕግ ስርጸትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት ዐቃቢ ህግ አቶ እስጢፋኖስ አበበ ስለ ሰብዓዊ መብቶች ምንነት፣መለያ ባህርያት እና የመንግስት ግዴታዎች ፣ በፖሊስነት ሙያ የስብአዊ መብቶች ጥበቃ ምን መምሰል እንዳልበት ሰፊ ግንዛቤ ሰጥተዋል፡፡
በሌላ በኩል በፖሊስነት ስራ የሰብዓዊ መብቶች ጥበቃ፣ከሰብዓዊ መብት ጋር በጥብቅ የሚገናኙ ዋና ዋና የፖሊስ ተግባራት፣ ከሰብዓዊ መብት ጋር ጥብቅ ግንኙነት ያላቸው ልዩ የምርመራ ዘዴዎች ላይ እና ስለ ተያዙ ሰዎች መብት ላይ ግንዛቤ የሰጡት ዐቃቢ ሕግ አቶ ሙሴ ባዬ ናቸው፡፡
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.