
በፍልሰተኞች ጉዳይ ላይ ትኩረት ያደረገ ውይይት በመደረግ ላይ ነው።
በፍልሰተኞች ጉዳይ ላይ ትኩረት ያደረገ ውይይት በመደረግ ላይ ነው።
።።።።።።።።
የካቲት 28 ቀን 2017 ዓ.ም
ፍትህ ቢሮ
በውይይቱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ አመራሮች ፣ የክ/ከ የፍትሕ ጽቤት ኃላፊዎች እንዲሁም ከከተማ እስከ ክፍለ ከተማ የትብብር ጥምረት ተጠሪዎች ተገኝተዋል።
የአዲስ አበባ ፍትህ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተክሌ በዛብህ የምክክር መድረኩን ያስጀመሩ ሲሆን በንግግራቸውም ህገ-ወጥ ፍልሰት ከግለሰብና ሀገር የወንጀል ስጋት ከመሆን አልፎ የቀጠናው ስጋት በመሆኑ የሚመለከተው አካል ሁሉ ጉዳዩን አቅዶ በመተግበር አፈጻጸሙን እየገመገሙ ስልት በመንደፍ መስራት ይፈለጋል ብለዋል።
ኃላፊው አክለው መንግስት የወንጀሉን አሳሳቢነት ያገናዘበ ሕጎችን በማውጣት እንዲሁም አለም ዓቀፍ ኮንቬንሽኖችን በመቀበል ተግባራዊ ለማድረግ የተለያዩ አደረጃጀቶችን በማዋቀር በመስራት ውጤታማ በማድረግ ላይ ይገኛል ብለዋል።
ወንጀሉን ለመከላከል የተሰሩ ስራዎች ምንም እንኳን የተሻሉ ቢሆንም ወቅቱን የዋጀ ተለዋዋጭነቱን ያገናዘበ ስራ መስራት ይጠበቃል በማለት የመድረኩ ተሳታፊዎች ወንጀሉ እጅግ የረቀቀ እና ተለዋዋጭ መሆኑን በመረዳት ስራን አጠናክሮ በመተግበር ወንጀሉን ለመቀነስ መስራት ይጠበቃል ብለዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ የትብብር ጥምረት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዮሃንስ ብርሃኑ በበኩላቸው በሰው የመነገድ ወንጀል እና ህገ-ወጥ ፍልሰት እጅግ አሳሳቢ እንዲሁም ማህበራዊ ፣ኢኮኖሚያዊ ችግር እየሆነ በአለም አቀፍ ደረጃም ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት እየተሰራ እንዳለ ገልጸው በሀገራችንም ይህንኑ ለመቅረፍ በርካታ የፓሊሲ ፣ የሕግ እና የአሰራር ማሻሻያዎች በማድረግ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማትን በማስተባበር ወንጀሉን ለመከላከል እየተሰራ እንዳለ ገልጸዋል።
ጽ/ቤት ኃላፊው የምክክር መድረኩ ለሁለት ቀን እንደሚቆይ እና በምክክሩ ወቅታዊ የፍልሰት ጉዳይእንዲሁም የ2017 የግማሽ ዓመት አፈጻጸም ቀርቦ ውይይት እንደሚደረግ አሳውቀዋል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.