የ2017 በጀት ዓመት የሁለተኛ ግማሽ ዓመት የቅ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የ2017 በጀት ዓመት የሁለተኛ ግማሽ ዓመት የቅንጅታዊ አሰራር ዕቅድ ክለሳና ግምገማ ተካሄደ።

የ2017 በጀት ዓመት የሁለተኛ ግማሽ ዓመት የቅንጅታዊ አሰራር ዕቅድ ክለሳና ግምገማ ተካሄደ። 
*****************
ITDB፦ መጋቢት2/2017 ዓ.ም 

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ እና ባለድርሻ አካላት የ2017 በጀት ዓመት የሁለተኛ ግማሽ ዓመት የቅንጅታዊ አሰራር ዕቅድ ክለሳና ግምገማ ተካሄደ። 

የመርሃ-ግብሩ ዋና ዓላማ በ2017 መጀመርያ ግማሽ ዓመት በቅንጅት ሲሰሩ የነበሩ ስራዎች አጠናክሮ ማስቀጠልና በክፍተት የታዩትን በማረም ዉጤታማ ስራ ለመስራት ሲሆን የመርሃ-ግብሩን መክፈቻ ንግግር ያደረጉት የቢሮ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ግሩም አብተዉ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክታቸዉን አስተላልፈዉ በ2017 በጀት ዓመት የጋራ ዕቅድ በማቀድ ወደ ስራ መገባቱን ገልፀዉ በዛሬዉ መርሃ-ግብርም በተዘጋጀዉ የጋራ ዕቅድ ላይ ዉይይት በማካሄድ መከለስና በቀጣይ በምን አግባብ እንስራ የሚለዉ ላይ ትኩረት የሚያደርግ ዉይይት ማካሄድ መሆኑን በማመላከት መልካም የዉይይት ግዜ ተመኝተዋል።
በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ እና በባለ ድርሻ አካላት መካከል የተደረገ የ2017 በጀት ዓመት የቀሪ ስድስት ወራት የቅንጅታዊ አሰራር ትስስር ስምምነት የተከለሰ ዕቅድ ያቀረቡት የቢሮ የለዉጥ ዳይሬክተር አቶ ግርማ ከበደ ሲሆኑ ሰነዱ ትኩረት ያደረገባቸዉ ርዕሰ ጉዳዮች የትስስር ሰነዱ ሁኔታ፣ አስፈላጊነት፣ መርሆዎች፣ ወሰንና ከቅንጅታዊ አሰራር የሚጠበቅ ውጤት፣ ሊያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮች፣ የመፍትሔ አቅጣጫዎች፣ ሚናዎች፣ ዉጤቶች፣ እና የድርጊት መርሃ-ግብር፣ የመግባቢያ ሰነዱ የተፈፃሚነት ወሰን እንዲሁም የጋራ ስምምነት ሰነዱን የተፈራረሙ ተቋማት ላይ ዝርዝር ማብራርያ ሰጥተዋል። በተያያዘም ተሳታፊዎቹ በቀረበዉ ሰነድ ላይ መሰረት ያደረገ ሀሳብ አስተያየት ያነሱ ሲሆን የቢሮ ጽ/ቤት ሀላፊና የሪፎርም ዳይሬክተር የተነሱ ሀሳብ አስተያየቶችን እንደግብዓት በመዉሰድ ምላሽ ሰጥተዋል። 

በመጨረሻም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር የ2017 በጀት ዓመት የቀሪ ስድስት ወራት የቅንጅታዊ አሰራር ትስስር ስምምነት የተከለሰ ዕቅድ በቢሮ ሀላፊ  አማካኝነት ተፈራርመዋል። 

ወቅታዊና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ዌብ ሳይት (website):https://www.aaitdb.gov.et   ፌስቡክ (Facebook page):https://www.facebook.com/AAITDB
ኢሜይል (Email): aaitdb@aaca.gov.et
መስመር ስልክ (Phon Number):+251-118547714


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.