
በ2017 በጀት ዓመት የ6 ወራት የፍትህ ዘርፍ ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ አፈጻጸም እና የግማሽ አመት አፈጻጸም ምዘና ውጤት ሪፖርት ውይይት ተደረገ፡፡
በ2017 በጀት ዓመት የ6 ወራት የፍትህ ዘርፍ ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ አፈጻጸም እና የግማሽ አመት አፈጻጸም ምዘና ውጤት ሪፖርት ውይይት ተደረገ፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
መጋቢት04/2017
በቢሮ እና ክፍለ ከተሞች የግማሽ አመት ፍትህ ትራንስፎርሜሽን ትግበራ ብሎም ቀጣይ ትኩረት ነጥቦች እና እቅድ አፈጻጸም ምዘና ዙሪያ ትኩረት ያደረገ ውይይት የፍትህ ቢሮ አመራሮች፣ የሁሉም ክፍለ ከተማ ፍትህ ጽ/ቤት ኃላፊዎች እና ዳይሬክተሮች በተገኙበት ተካሂዷል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተክሌ በዛብህ የ2017 በጀት ዓመት የ6 ወራት የፍትህ ዘርፍ ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ያቀረቡ ስሆን በግማሽ ዓመት ከተከናወኑ ተግባራት የፍትህ ዘርፋን አመራርና ባለሙያዎችን ማጥራት፣ የማህበረሰብ አቀፍ ፍትህ አገልግሎት የሚያጠናክር ማህበራዊ ፍርድቤቶችን አደረጃጀትና አሰራር በማሻሻል ማጠናከር፣ አገልግሎት እየሰጡ ያሉ የመሠረተ-ማህበረሰብ አገልግሎት ተቋማትን በጥናት መለየትና ለተለዩት ሕግ ማዕቀፍ አዘጋጅቶ እውቅና መስጠት፣ውጤታማ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መሠረት የሚጥሉ የአይሲቲ መሠረተ ልማት ማጠናከር አገልግሎቶችን የሚያቀላጥፉ ሶፍትዌሮችን ማበልጸግ የበለጸጉትን በመጠቀም ሥራዎችን ማዘመን፣በተለይ በአሰራር እና በግብዓት በአደረጃጀት ያሉ ችግሮች እንዲፈቱ የማድረግ ስራዎች መስመር እየያዙ መምጣታቸውን አንስተዋል።
ከህግ ማዕቀፍ ጋር ተያይዞ የሚነሱ ክፍተቶችን እና ችግሮች እንዲፈቱ የተለየ ትኩረት ተሰጥቶት በበጀት ዓመቱ የታቀዱ የተከናወኑ ተግባራት መሆናቸውንም ገልጸዋል፡፡
ኃላፊው አክለውም ለሰራተኛው ምቹ ሁኔታ ከመፍጠር አንጻር፣ ስራ ላይ ያሉ አሰራርና አደረጃጀት በመፈተሽ ማስተካከል፣ የቴክኖሎጂ ትግበራ፣ የመሰብሰቢያ አዳራሽ እድሳት የመሳሰሉ ተግባራት መከናወናቸውን አብራርተዋል።
የ2017 የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት የዕቅድ አፈፃፀም ምዘና ውጤት ሪፖርት ያቀረቡት የለውጥና መልካም አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ተወካይ የሆኑት አቶ ሰቦቃ ገመቹ ሲሆኑ የምዘናው ዋና ዓላማዎች ምዘናው ያተኮረባቸው ዋና ዋና ጉዳዮች የተቋሙን የአገልግሎት አሰጣጥ ውጤታማነት፣የሪፎርም ስራዎች አፈፃፀም እና የመደበኛ ስራዎች/እቅድ አፈፀፀም ላይ ትኩረት አድርጎ አቅርበዋል፡፡
በተጨማሪም በምዘናው ወቅት የተገኙ ተጨባጭ ጥንካሬዎች እና የተስተዋሉ ቁልፍ ውስንነቶችን በማቅረብ በምዘናው ወቅት የተስተዋሉ ድንቅ አሰራሮች ትኩረት የሚፈለጉ ጉዳዮች ዳሰሳ ተደርጓል፡፡
በመጨረሻም በወጡ ህጎች ተደራሽነት፣ ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ቀጣይ ትኩረት አቅጣጫ፣ ከቴክኖሎጂ ትግበራ እና ሌሎች ከቤቱ ለተነሱት ጥያቄዎች የቢሮ ኃላፊ ምላሽ በመስጠት ተጠናቋል፡፡
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.