
በሰብአዊ መብት ላይ ያተኮረ ስልጠና መሰጠት ተጀመረ
መጋቢት 8 ቀን 2017
ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ እና የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ድርጅቶች ህብረት (ሲኢህሮ )ከአዲስ አበባ ፖሊስ ጋር በመተባበር በሰብአዊ መብት እና የፖሊስ አገልግሎት ዙሪያ የሁለት ቀናት የስልጠና መርሃ ግብር ጀምረዋል።
ስልጠናው ሰብዓዊ መብቶች ምንድን ናቸው ፣ በአከባባዊ እና በአለም ሰብዓዊ መብት ምን ይመስላል ፣ሰብዓዊ መብቶች በኢትዮጵያ ምን ይመስላል በሚል ይሰጣል።
የህግ አስከባሪ አካላት መደበኛ ስራቸውን በሚሰሩበት ወቅት፣ የፖሊስ አካላት የህዝብ ፀጥታ ጠባቂ ብቻ ሳይሆኑ መሰረታዊ ሰብአዊ መብቶች እና የዜጎች ነፃነት ጠባቂዎች እንደመሆናቸው መጠን ምን ተግባራት እየተተገበረ ይገኛል በሚል የመወያያ መድረክ ይሆናል።
በሌላ በኩል ስልጠናው የህዝብን ደህንነት በማረጋገጥ ሰብአዊ መብቶችን እንዴት ማስከበር ይችላል የሚለውን አንገብጋቢ ጥያቄ መርማሪ ፖሊሶችን እና አቃብያነህግ ተጠያቂነትን ለማጎልበት ያለውን ወሳኝ ሚና በመዳሰስ የሰብአዊ መብቶች መርሆዎች በንድፈ ሀሳባዊ ብቻ ሳይሆን በተግባር ያለውን አሰራር ለመወያየት የሚያስችል ስልጠና ይሆናል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.