በሴቶች  መብት  ዙርያ ስልጠና ተሰጠ፡፡

image description
- ውስጥ Laws    0

በሴቶች  መብት  ዙርያ ስልጠና ተሰጠ፡፡

08/07/2017  

ስልጠናው የተሰጠው   በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ የሕግ ስርጸትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት  ለቢሮው ሴት ሰራተኞች እና ለሴት መምህራን በሴቶች ነው።

በወቅቱ የአዲስ አበባ ከተማ ፍትሕ ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ አሰፋ መብራቴ በመክፈቻ ንግግራቸው መንግስት በሴቶች ሁለንተናዊ ተሳትፎ ላይ ትኩረት በመስጠት እየሰራ ነው በማለት ሴቶችን በፖለቲካው ፣ በማህበራዊ እና በኢኮኖሚው ዘርፍ በማሳተፍ ትልቅ ለውጥ መጥቷል ብለው እንደተቋማችንም ይህንን አጠናክረን እያስቀጠልን እንገኛለን ብለዋል ።

ኃላፊው አክለው ሴቶችን የማብቃት ስራ የሪፎርሙ አካል በመሆኑ የተለያዩ የግንዛቤ ማስጨበጫ  ስልጠናዎችን በማከናወን ሴቶችን የማብቃት ስራ እየተሰራ እንደሆነ  ገልጸው  ሌሎች ሴቶችን ማዕከል ያደረጉ ተግባራት እየተሰራ መሆኑን ገልጸው ስልጠናውን ከፍተዋል።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ የሕግ ስርጸትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት ወይዘሪት  ብርሃን ደመቀ  ስለሴቶች መብት፣የሴቶች እኩልነት መብት፣የሴቶች መብት ከዓለም አቀፍ ህጎች አንፃር፣የሴቶች መብት በኢፌዴሪ ህገ-መንግስት እና በሴቶች ላይ የሚፈጸሙ የሀይል ጥቃቶች ዙርያ ሰፊ ግንዛቤ  ሰጥተዋል፡፡

ዳይሬክተሯ ሴቶች በየትኛውም ማህበረሰብ ክፍል ውስጥ ለአድልኦ የተጋለጡ እንደሆኑ በመግለጽ ለዚህም ምክንያት የሆነው ጎጂ ልማዶች፣ ኃላ ቀር  አመለካከቶች፣ በቤተሰብ፣ በህብረተሰቡ ፣በስራ ቦታ ባሉ ምክንያት ሊሆን እንደሚችል በማንሳት እኩልነታቸውን ለማረጋገጥና ይደርስባቸው የነበረውን ተጽኖ ለመቅረፍ  የሴቶችን እኩልነት በተለያዩ ህጎች እውቅና መስጠት ወሳኝ ነው ብለዋል፡፡ 

ሀገራችን ኢትዮጵያም የተባበሩት መንግስታት አባል ሀገር በመሆኗ በዓለም አቀፍ ደረጃ የተቀበለቻቸውን ስምምነቶች በህገ-መንግስቷ በመደንገግ ተጨማሪ የማስፈፀሚያ ህጐችን በማውጣት ጭምር የሴቶች የእኩልነት መብት ለማስከበር ጥረት እያደረገች ስለመሆኗ  ከስልጠናው ማረጋገጥ ተችሏል፡፡ በመጨረሻም ከተሳታፊዎች በሴቶች መብት፣በድጋፍ እርምጃ(Affirmative actions) እንዲሁም በጋብቻ ዙርያ የተለያዩ ሃሳብ አስተያየት በማንሳት ዐቃቢ ሕጓ ምላሽ በመስጠት ስልጠናው ተጠናቋል፡፡


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.