የፌዴራል ፍትህና ሕግ ኢንስቲትዩት ከፍትህ ቢሮ...

image description
- ውስጥ Laws    0

የፌዴራል ፍትህና ሕግ ኢንስቲትዩት ከፍትህ ቢሮ ጋር በመተባበር ለዐቃቢያነ ሕግ ሲሰጥ የነበረው የመጨረሻውን ዙር ዛሬ ጀምሯል።

መርሐ ግብሩ ላይ የፌደራል ፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት በሚንስትር ድኤታ ማዕረግ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ዘካሪያስ ኤርኮላ ፣የአዲስ አበባ ፍትህ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተክሌ በዛብህን ጨምሮ ሌሎች በየደረጃው ያሉ አመራሮች ተገኝተዋል።

የፌደራል ፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት በሚንስትር ድኤታ ማዕረግ ምክትል ዋና ዳይሬክቴር አቶ ዘካሪያስ ኤርኮላ አቶ በማጠቃለያ ንግግራቸው በፍትህ  ዘርፉ የእያንዳንዳችን ድምር ውጤት በመሆኑ ፍትህ ዘርፉ ላይ ያለውን ስብራት ለማስተካከል  አስተዋፅኦ ማበረከት ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡

ዋና ዳይሬክተሩ በሌላ በኩል ኢኒስቲትዩቱ ለዳኝነት አካሉ እና ለሌሎች ፍትህ አካላት ገለልተኛነታቸውን በጠበቀ መልኩ ስልጠናዎችን እየሰጠ እንደሆነ በማንሳት በተለይ የአዲስ አበባ ከተማ ፍትህ ቢሮ የሚንሰጣቸው ስልጠናዎች ተግባር ተኮርና ከንድፈ ሐሳብ በዘለለ ስራ ላይ የሚውሉ በመሆናቸው

በተለየ ትኩረት እየሰራን እንገኛለንም ብለዋል፡፡   

የአዲስ አበባ ፍትህ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተክሌ በዛብህ በበኩላቸው ከተማ አስተዳደሩ የተቋማትን አደረጃጀት ፣ የአሰራር ስርዓት ብሎም የተለያዩ መሰረተ ልማቶችን በማሻሻል 7/24  ሳምንቱን ሙሉ በመስራት እምርታዊ ለውጥ የሚገኝ በመሆኑ ፍትህ ቢሮ በዚሁ ልክ ለመጓዝ ህግን እና ስርዓትን የሚያከብር የነቃ ማህበረሰብን ለመፍጠር የበቃ ባለሙያ እና የተገነባ ተቋም አስፈላጊ በመሆኑ በዘርፋ መጠነ ሰፊ ስራዎችን እየሰራን  እንገኛለን ብለዋል፡፡

 

ኃላፊው አክለው በከተማ አስተዳደሩ ያላችሁ አቃቢያነ ህግ ቢሮአችን የከተማ አስተዳደሩ ዋና የህግ አማካሪ እንዲሁም የህዝብ እና የመንግስት ጥቅም ለማስጠበቅ እንደሚሰራ የህግ አካል በየትኛውም ዘርፍ በልዩ ትኩረት ከቀደመው የበለጠ በመልካም ስነምግባር እና በትጋት መስራት ከሁሉም ይጠበቃል በማለት አሳስበዋል፡፡

ስልጠናው በኮንስትራክሽን ህግ፣ በወንጀል ስነ-ስርዓት፡- (ክስ አመሰራረትና የክርክር ሂደት አመራር ፣ የፍታሐብሄርስነ-ስርዓት ህግ (አቤቱታ አዘገጃጀት፣የክርክር አመራር፤ የይግባኝና የሰበር አቤቱታ ፣ ለህዝብጥቅም ሲባል ስለሚለቀቅ ንብረት (law of expropriation for public use ፣በመሬት ይዞታ ላይ የሚነሱ ክርክሮች አድማስ ላይ መሰጠት ከጀመረ 5ተኛ ዙር እንደሆነ ለማወቅ ችለናል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.