
ቢሮው የረመዳን ጾምን ምክኒያት በማድረግ የኢፍጣር መርሃ ግብር አካሄደ።
አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትሕ ቢሮ የረመዳን ፆምን ምክኒያት በማድረግ ከክ/ከተማ ፍትሕ ፅ/ቤት ኃላፊዎችና የቢሮ ዐቃቢያነ ሕግ እና ሰራተኞች እንዲሁም ጥሪ ከተደረገላቸው የእምነቱ ተከታዮች ጋር በጋራ በመሆን የኢፍጣር ስነስርዓት አካሂዷል፡፡
በኢፍጣር ስነ-ስርዓቱ ላይ መልክታቸውን ያስተላለፉት የፍትህ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተክሌ በዛብህ እንደተናገሩት ሀገራችን ብዝሀ ሀይማኖት ተከታዮች ተከባብረው እና ተሳስበው የሚኖርባት ሀገር እንደመሆኗ መጠን ተከባብረው፣ ተዋዶና ያለው ለሌለው የማካፈል የጋራ እሴቶቻችን ይበልጥ የሚጎላበት የጾምና የጸሎት ወራት ላይ ስለሆንን ይሄው መልካም ልምምድ ባህል መሆን እንዳለበት አንስተዋል።
ኃላፊው አክለው ዛሬ በተቋማችን ካሉት የእምነቱ ተከታዮች ጋር ስናሳልፍ ኢትዮጵያዊ ወንድማማችነታችንና አብሮነታችንን ለመግለጽ ነው በማለት ለእምነቱ ተከታዮች መልካም የረመዳን ወር እንዲሆንላቸው የመልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል ፡፡
ፍተሕ ቢሮ፤ መጋቢት 16 ቀን 2017 ዓ.ም
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.