በሙያ እና በስራ ስነ-ምግባር ዙሪያ ስልጠና ተሰ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

በሙያ እና በስራ ስነ-ምግባር ዙሪያ ስልጠና ተሰጠ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ የስነ-ምግባርና በፀረ-ሙስና መከታተያ ዳይሬክቶሬት  ለፍትህ ቢሮ ሰራተኞች በሙያ እና በስራ ስነ-ምግባር ዙሪያ ስልጠና ሰጠ፡፡

በስልጠናው እለት የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ የጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ግርማ ወርቁ ስነ-ምግባር ሰፊ ትርጉምና ለተቋም ብሎም ለሀገር ጠቀሜታ ያለው ፅንሰ-ሀሳብ መሆኑን ጠቅሰው ከቤተሰብ እስከ ሀገር ተፅዕኖ የሚፈጥር እንደሆነ ገልፀዋል፡፡  በተጨማሪም የጽ/ቤት ኃላፊው ስነ-ምግባር በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ ሰፊ የሆነ ጠቀሜታ እንዳለው በመግለፅ የቢሮወ ሰራተኞች ስልጠናውን በስነ-ምግባር በአግባቡ እንዲከታተሉ በማሳሰብ ስልጠናውን በይፋ ከፍተዋል፡፡

ስልጠናውን የሰጡት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ የስነ-ምግባርና የፀረ-ሙስና መከታተያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ሲሳይ በፍቃዱ ናቸው፡፡

ስልጠናው አምስት ተያያዥ ሀሳቦች ላይ ማለትም  ስለ ስነ-ምግባር ምንነት፣ ስለ ስነ-ምግባር ምንጮች/ መሰረቶች፣ ስለ ስራና ሙያ ምንነት፣ ስለ ስራና ሙያ ስነ-ምግባርና ፋይዳው/ጠቀሜታው እንዲሁም ሌሎችም ተዛማጅ ርዕሰ-ጉዳዮች ላይ ሰፊና አሳታፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

በመጨረሻም የስልጠናው አጠቃላይ ሂደት ጥሩ እንደነበር በማመስገን  የገለጹት ተሳታፊዎቹ  ለተነሱት ሃሳብና አስተያየቶች አቶ ሲሳይ በፍቃዱ ምላሽ በመስጠት ስልጠናው ተጠናቋል፡፡


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.