
ቢሮው መጪውን የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ ማዕድ የማጋራት መረሃ ግብር አከናወነ።
በመርሃ ግብሩ ሁለት መቶ ሰላሳ አምስት የሚደርሱ ወገኖችን ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል ።በዕለቱ የፍትህ ቢሮ የስራ ኃላፊዎች በስፍራው ተገኝቶ ኩነቱን የመሩ ሲሆኑ ለበዓል መዋያ የሚሆኑ የተለያዩ ቁሳቁሶችና ቢሮው ለሚያሳድጋቸው ሰባት ህጻናት በተጨማሪም የጥሬ ገንዘብና ስጦታ ተበርክቶላቸዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተክሌ በዛብህ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ባስተላለፉበት ወቅት የእርስ በርስ መተሳሰብና መደጋገፍ ነባር የኢትዮጵያዊያን ባህል ከመሆኑም ከቅርብ አመታት ወዲህ ሰው ተኮር ተግባራት ታስቦና ታቅዶ አየተተገበረ ያለና ልቀጥል የሚገባ ወሳኝ ስራ በመሆኑ እኛም ይህንን በማሰብ በዓሉን በደስታ እንዲያሳልፉ አብሮነታችንን ለመግለጽ ማዕድ እንዲጋሩ አድርገናል ብለዋል።
ኃላፊው አክለውም በዓሉን ስናሳልፍ በማህበራዊ ችግር ውስጥ ያሉ ወገኖቻችን በኢትዮጵያዊ መተሳሰብና መደጋገፍ ያለንን በማካፈል ፍቅራችንና ትህትናችንን በመግለፅ መሆን እንዳለበትም አሳስበው መርሃ ግብሩን ላስተባበሩ ኮሚቴዎች፣ ድጋፍ ላደረጉ አካላት በሙሉ በቢሮው ስም ምስጋና በማቅረብ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክታቸው አስተላልፈዋል፡፡
ድጋፍ የተደረገላቸው ወገኖችም ስለተደረገላቸው ድጋፍ በማመስገን ለመላው የበአሉ ተሳታፊዎች መልካም የትንሳኤ በዓል እንዲሆን ምኞታቸውን ገልጸዋል።
ሚያዝያ 07/2017
ፍትህ ቢሮ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.