
የክርክር ሂደቶች በዕውቀትና በስነ-ምግባር መምራት እንደሚገባ ተገለጸ፤
ይህ የተገለጸው በቢሮው የሕግ ክርክር ዘርፍ የ2017 በጀት ዓመት የ9 ወር አፈፃፀም ሪፖርት ገመገመበት ወቅት ነው፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ የህግ ጉዳዮች ክርክር ዘርፍ የ9 ወራት አፈጻጸም ከክ/ከተማ የክርክር እና የወንጀል ዳይሬክተሮች በተገኙበት ተገምግሟል።
የፍትህ ቢሮ ምክትል ሃላፊ አቶ ተስፋዬ ደጀኔ የገለጹት ግምገማውን ባስጀመሩበት ወቅት"ዐቃቢ ሕግ ለፍትህ የቆመ ነው" በማለት ዜጎች በሕግ እይታ በእኩል መታየት እንዳለባቸው እና የዜጎች መብት እንዳይጣስ ተጠያቂነትን የሚሰያን ተቋም መገንባት ያስፈልጋል ብለዋል።
ኃላፊው የክርክር ሂደቶች በዕውቀትና በስነ-ምግባር መምራት እንደሚገባ ገልጸው ግምገማው ክርክር እንዴት ሲመራ እንደነበረ ፣ የመንግስትን እና የህዝብን ጥቅም ከማስጠበቅ አንጻር በተለይ ህገወጥ የመሬት ወረራን ፣ የመንግስት ቤቶች እንዲሁም ሜጋ ፕሮጀክቶች አሰመልክቶ እግዶች እንዴት እንደተመሩ እንዲሁም ሰብአዊ መብትን ከመጠበቅ አንጻር ምን ታቅዶ እንደተከናወነ የሚያሳይ ግምገማ መሆን እንዳለበት አቅጣጫ በመስጠት አስጀምረዋል ።
በወቅቱ ከየክፍለከተሞች የመጡ የፍታብሔር ዳይሬክተሮች እና ወንጀል ዳይሬክተሮች አጠቃላይ የ9ወራት አፈፃፀማቸውን ከአበይት ተግባራት አንፃር በነበረ ጠንካራ እና ደካማ ጎን እንዲሁም በቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ አንፃር አቅርበዉ ዉይይት የተደረገበት ሲሆን የእቅድ አፈጻጸም ግምገማው በክ/ከተሞች መካከል መማሪያና ልምድ ልውውጥ የሚፈጥር መሆኑ የመድረኩ ተሳታፊዎች ገልጸዋል።
ኃላፊው በማጠቃለያ ንግግራቸው ካለፈው አፈጻጸም አንጻር ሲታይ የተሻለ አፈጻጸም መሆኑን ገልጸው ለቀጣይ ቀሪ ወራቶች የታቀዱት ተግባራት እንዲሳኩ ትኩረት ተሰጥቶት መሠራት አለበት ያሉት በተለይ፦ በወንጀል አፈጻጸም በዕርቅ ከመጨረስ አኳያ ፣ዉጤታማ ክርክር ማድረግ፣ በተጨማሪም የመንግስት የልማት ፕሮጀክቶች ፣ የመሬት ወረራ እና ህገወጥ ግንባታዎች እንዲሁም የመንግስት ቤቶች አስመልክተው የሚደረገው የፍ/ቤት ክርክሮች ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት መመራት ያለባቸው መሆኑን አስገንዝበዋል።
በተጨማሪም ከተቋማት ጋር ተቀናጅቶ መስራት ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባ በተለይ ክርክሮች ሲመሩ በዕውቀትና በስነ-ምግባር መምራት እንደሚገባ ያስፈልጋል ሲሉ ገልጸዋል፡፡
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.