ቢሮው ከ2.2 ቢሊየን ብር በላይ የሚገመት የህዝ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ቢሮው ከ2.2 ቢሊየን ብር በላይ የሚገመት የህዝብ ጥቅም ማስጠበቅ ችሏል ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ በ2017 በጀት ዓመት የ9 ወራት ዕቅድ አፈፃፀሙን የቢሮውና የተጠሪ ተቋም አመራሮች እና ስራ ክፍሎች ሀላፊዎች በተገኙበት ገምግሟል።

በዕለቱ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተክሌ በዛብህ በዘጠኝ ወራት አፈፃፀም የታዩ ጠንካራ ጎኖችን በማስቀጠል እንዲሁም ክፍተቶችን በመለየት ተናቦና ተቀናጅቶ በልዩ ተነሳሽነት በመስራት በተቀሩት ሶስት ወራት የአመቱ አፈጻጸም ከእቅድ ጋር የተስተካከለ ወይም ብልጫ ማሳየት ይጠበቅብናል ብለዋል።

በቢሮው የእቅድና በጀት ዝግጅት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ደሳለኝ በላይ እቅድ አፈጻጸሙን ያቀረቡ ሲሆን በይዘትም በፍትሐ-ብሄር ጉዳዮች የከተማ አስተዳደሩን የነዋሪውን መብትና ጥቅም ከማስጠበቅ ፣ የህግ ኦዲት ውጤታማነት ከማሳደግ አንፃር ፣ ከሰብዓዊ መብት ማስከበር፣ በሰው መነገድና ሰውን በህገወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር ወንጀልን ከመከላከል ፣ ከወንጀል ህግ አፈፃፀም ፣ የህግና ፍትህ ማሻሻያ ስራዎችን ከማሳደግ፣ የሰው ሃብት አስተዳደር ስራዎችን፣ የኢንፎርሜሽን ኮምኒኬሽን እና ቴክኖሎጂ አሰራርንና ውጤታማነት ከማሳደግ፣ የህዝብ ግንኙነት ስራዎችን እንዲሁም የታክስ ይግባኝ በቀረቡ መዝገቦች ፈጣን ፍትህ ከማስፈን አንጻር የተሰሩ ስራዎች ያጋጠሙ ችግሮች ፣የተወሰዱ የመፍትሔ እርምጃዎች እና የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ሰፋ ባለ መልኩ አቅርበዋል ።

አቶ ደሳለኝ አክለውም ቢሮው  በሚያደርገው ክርክሮች ያስጠበቀው የመንግስት ጥቅም በገንዘብም ሆነ በአይነት እያደገ በመምጣቱ ተገልጋዮችም ሆነ የከተማ ነዋሪዎች በፍትህ ቢሮ ላይ ያላቸው እምነት እያደገ መምጣቱን በመግለፅ  በር9ወራት ውስጥ 2,270,401,470.64 (ሁለት ቢሊዮን ሁለት መቶ ሰባ ሚሊየን አራት መቶ አንድ ሺህ አራት መቶ ሰባ ብር ከ64 ሳንቲም ) ብር በገንዘብ የሚተመን የመንግስት እና ህዝብ ጥቅም ማስጠበቅ እንደተቻለ እና ጥቅል የዕቅዱ 96.526 % ማሳካት መቻሉን ሪፖርት ባቀረቡበት ወቅት ገልጸዋል ።

በመጨረሻም በቀጣይ ቀሪ ወራት  የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም የተሻለ እንዲሆን የነበሩ ጉድለቶች በማረም ፣ የተነሱ ጥያቄዎችና የተሰጡ አስተያየቶችን እንደ ግብዓት በመውሰድ ከባለፈው ዓመት ውጤታማና ጥሩ ደረጃ ለማምጣት የከተማ  አስተዳደሩና የነዋሪውን መብትና ጥቅም በማስጠበቅ ቀጣይነት ያለዉ የተጠያቂነት ስርዓት በማስፈን የነበሩ ተግዳሮቶችን በተሻለ ጥራትና ብቃት መተግበር  ያስፈልጋል ያሉት የቢሮው ኃላፊ አቶ ተክሌ በዛብህ ለተነሱ ጥያቄዎች እና አስተያየቶች ምላሽ በሰጡበት ወቅት ነው።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.