የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስ የሰው ሃብት ልማት ቢሮ በፍትሕ ቢሮ በመገኘት ክትትልና ድጋፍ አደረገ፡፡

በክትትል ድጋፉ ወቅት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ ዳይሬክተሮች እና ጽ/ቤት ሃላፊዎች የተገኙ ሲሆን ከፐብሊክ ሰርቪስ የሰው ሃብት ልማት ቢሮ በመጡ በአገልግሎት አሰጣጥና አውትሶርሲንግ ዘርፍ የአገልግሎት አሰጣጥ ክትትል ድጋፍ ዳይሬክቶሬት ተገኝተው በፍትህ ቢሮ ያለውን ነባራዊ ሁኔታ አይተዋል፡፡

የክትትሉ ዓላማ የ2017 በጀት አመት የ3ተኛ ሩብ ዓመት የመደበኛ ክትትልና ድጋፍ ማድረግ እና በአገልግሎት አሰጥጥ ላይ ምን ምን ስራዎች እንደተሰሩ ለቀጣይ ቀሪ ወራቶች አቅም ፈጥሮ ለመገኘት እንደሆነ ተገልጿል፡፡

ክትትልና ድጋፉ የግማሽ በጀት ዓመት እቅድ ክለሳና አፈጻጸም ግምገማ በተመለከተ፣ በአገልግሎት አሰጣጥ ማኑዋል መሰረት የተደራጁ አደረጃጀቶች የውይይቶች ያለበት ሁኔታ በተመለከተ፣ ለሰራተኞች ምቹ የስራ አካባቢን ከመፍጠር አኳያ፣ የግልጸኝነትና ተጠያቂነት ከመፍጠር አንጻር፣ አገልግሎቶችን በቴክኖሎጂ ከማስደገፍ በተመለከተ፣ ተቋማዊ መማማርን ማጎልበት (የሰራተኛ አቅም ግንባታ)፣ ምርጥ ተሞክሮ መቀመርና ማስፋት፣ የክትትልና ድጋፍ አግባብ በተመለከተ ክትትልና ድጋፍ ተደርጓል፡፡

በመጨረሻም ፍትህ ቢሮ ብዙ መሻሻሎችና ለውጦች  እንዳሉ በመግለጽ የታዩትን ክፍተቶች በፍጥነት በማረም ጥንካሬን ማስቀጠል እንደሚያስፈልግ አጽኖት ተሰቶት መሰራት እንዳለበት አቅጣጫ በማስቀመጥ መድረኩ ተጠናቋል።

ሚያዝያ 21/2017


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.