
በከተማ አስተዳደሩ ተፈጻሚነት ያላቸውን ህጎች አፈጻጸማቸውን መከታተል እንደሚገባ ተገለጸ፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ የህግ ስርፀት ምክር መስጠት እና የህግ ጥናት ፣ምርምርና ረቂቅ ዝግጅት ዘርፍ የክፍለ ከተማ የስርፀት ዳይሬክቶሬቶች እና የአዲስ ቲቪ ባለሙያዎች በተገኙበት የ2017 በጀት ዓመት የ9 ወር እቅድ አፈጻጸም ገምግሟል።
የቢሮው ምክትል ኃላፊ እና የዘርፉ ኃላፊ አቶ አሰፋ መብራቴ በታቀደው መሰረት አፈጻጸም መገምገም የነበሩ ጥንካሬዎች ለማስቀጠል ጉድለቶችን ለማረም ለቀጣዩ ለመዘጋጀት ያስችል ዘንድ ክፍተቶቻችንን በመሙላት እንዲሁም እየተካሄደ ያለውን የከተማችንን የህግ ትራንስፎርሜሽን እቅድ ለማከናወን የሚያግዝ ነው ብለዋል።
በህግ ስርፀት ዘርፍ የተሰሩ ስራዎችን የህግ ስርፀት ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት ዐቃቢ ሕግ ብርሃን ደመቀ ያቀረቡ ሲሆን በሪፖርቱም የከተማ አስተዳደሩ ነዋሪና አስፈፃሚ አካላት ንቃተ-ሕግ ማሳደግ ፣ የከተማ አስተዳደሩ ነዋሪና አስፈፃሚ አካላት የሕግ ምክር አገልግሎትን ማሳደግ በተመለከተ ፣አስተዳደራዊ ውሳኔዎች ከህግ ጋር የተጣጣመ መሆኑን ማረጋገጥ በተመለከተ ፣በአስተዳደሩ የወጡ ሕጎችና ተፈፃሚነት ማረጋገጥ በተመለከተ፣ የህግ አገልግሎት ለተፈቀደላቸውና ክርክር ለማያደርጉ ተቋማት ድጋፍና ክትትል ማድረግ በተመለከተ ፣ የተቋም ግንባታ ሥራ /ምቹ አከባቢን መፍጠርን/ በተመለከተ፣ የፍትህ አካላት ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ አፈጻጸም በተመለከተ ያጋጠሙ ችግሮች እና የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ ዘርዘር ባለ መልኩ አቅርበዋል፡፡
የህግ ጥናት ምርምርና ረቂቅ ዝግጅት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጀማል ሳላህ በ2017 ዓ.ም በ9 ወራት ውስጥ በዕቅዱ መሰረት የከተማው አስተዳደር አገልግሎት አሰጣጡን ለማሻሻል እያከናወነ ለሚገኘው ሪፎርም ስራ እና የኮሪደር ልማት ወሳኝ የሆኑ የተለያዩ ሕጎችን በማርቀቅና በሚመለከታቸው አካላት እየጸደቁ ተፈጻሚ እንዲሆኑ በማድረግ አኳያ በርካታ ተግባራት እንደተከናወነ ገልጸዋል፡፡
አቶ ጀማል አክለውም በአገር አቀፍ ብሎም በከተማችን እየተካሄደ ለሚገኘው የፍትህ ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ አተገባበር ፣ አዲስ ሕጎችን በማዘጋጀትና ነባር ሕጎች እንዲሻሻሉ በማድረግ በኩል ዳይሬክቶሬቱ የተሳካ ስራ እንደተሰራ በመግለጽ ሰፋ ባለ መልኩ ሪፖርት አቅርበዋል፡፡
በመጨረሻም በ9 ወሩ የነበሩ ጠንካራና ደካማ ጎኖችን በቀረበው ሪፖርት ዙርያ ከተሳታፊዎች ለተነሱት ጥያቄዎች የዘርፉ ኃላፊ እና ዳይሬክተሮች ምላሽ የሰጡ ሲሆን መድረኩን የመሩት የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ አሰፋ መብራቴ አፈፃፀሙ ከባለፈው ሲነፃፀር የተሻለ እንደነበር በመግለጽ የፍትህ ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ አተገባበር ፣አስተዳደራዊ ውሳኔን መፈተሽ እንዲሁም የህጎች ተፈጻሚነት መከታተል እንደሚገባ በሚሉት ጉዳዮች ላይ ለቀጣይ ቀሪ ወራት በትኩረት መስራት ይገባል ሲሉ በማጠቃለያ ንግግራቸው ገልጸዋል፡:
ሚያዝያ 28/2017
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.