
ቢሮው ከባለ ድርሻ አካላት ጋር የ2017 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወራት የቅንጅት ስራዎችን አፈፃፀም ገመገመ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ በ2017 በጀት አመት የዘጠኝ ወራት ቅንጅታዊ ስራዎች አፈፃፀሙን የቢሮው ከፍተኛ አመራሮች ፣በቅንጂት ለመስራት የተሳሰሩ በከተማ የአስተዳደሩ የተቋማት ሀላፊዎች፣ የክፍለ ከተማ ፍትህ ጽ/ቤት ሀላፊዎች እና የተለያዩ ሲቪክ ማህበራት ተወካዮች በተገኙበት የ9 ወራት ቅንጅታዊ ስራ በጋራ ገምግመዋል ፡፡
በወቅቱ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተክሌ በዛብህ ፍትህ ቢሮ ከተሰጠው ሀላፊነት አንጻር ባለፋት ዘጠኝ ወራት በሕግ ጉዳዮች የአስተዳደሩ ተቋማት አማካሪነቱንና ውክልናውን በተገቢው በመወጣት መብትና ጥቅም እያስጠበቀ እንደሚገኝ በመግለጽ ለመንግስት የተከበረ ከ 3098 በፍርድ ቤት ውሳኔ ካገኙ መዛግብት 2,873 በመርታት፣ በአይነት 230 ቤቶች፣ 56 መስሪያ ቦታ ሸዶች እና 198 ሄክታር መሬት በአጠቃላይ በ9 ወራት ውስጥ በብር ሲገመት 2,270,401,470.64 የመንግስትን እና የህዝብ ጥቅም ማስጠበቅ ተችሏል ብለዋል።
ኃላፊው አክለውም በውሎች አስተያየትና የውሎች ይረቀቅልኝ ጥያቄዎች ከማስተናገድ አንጻር 411 የውል አስተያየት፣ 384 ውሎች ረቂቅ ማዘጋጀት ተችሏል በማለት የከተማ አስተዳደሩ አስፈፃሚ አካላትና የነዋሪውን ንቃተ ሕግ ለማሳደግ መጠነ ሰፊ ስራ እንደተሰራ በሚዲያና በመድረክ ከ100% በላይ መፈጸም መቻሉን ገልፀው በክፍተት የተስተዋሉትን ነቅሶ በማውጣት በቀሪ ወራት ርብርብ እንደሚደረግ ገልጿል፡፡
በሪፖርቱ በዋናነት የፍትሕብሔር ጉዳዮች ክርክር በፍ/ቤት የመርታት አቅም ከማሳደግ አንፃር፣የወንጀል መዝገቦች ምርመራ እና የማጥራት ውጤታማነት ፣ የከተማ አስተዳደሩን ነዋሪና አስፈፃሚ አካላት ንቃተ ሕግ ከማሳደግ፣ አስተዳደራዊ ፍትህ ውጤታማነትና ማሳደግ፣ የህግና ፍትህ ስራዎችን ለማሻሻል ሕግ ጥናት ከማድረግ፣ ከሰብአዊ መብት ማክበርና ማስከበር አፈጻፀምን ከማሳደግ፣በሰው መነገድ እና ሰውን ሰውን በህገወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር ወንጀል ቁጥጥር ውጤታማነትን ከማሳደግ በዘጠኝ ወራት ተለይተው የተፈቱ የመልካም አስተዳድር ችግሮች፣ውጤቶቹ የተገኙበት አግባብ እንዲሁም ቢሮው ከተለያዩ አስፈፃሚ ተቋማት ጋር በቅንጅት የተሰሩ ስራዎች የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርት እና ተቀናጅቶ በመስራት የተገኙ ዋና ዋና ውጤቶች በተመለከተ የፍትህ ቢሮ አማካሪ በሆኑት አቶ አስመራ በዳዳ ከሰፊ ማብራሪያ ጋር አቅርቧል።
የፍትህ ቢሮ ምክትል ኃላፊና የሕግ ጥናት ረቂቅ ዝግጅትና ምክር መስጠት ዘርፍ ሀላፊ የተነሱት ሃሳቦች ገንቢ መሆናቸውን በመግለጽ እያንዳንዱ የወጡት ሕጎች ለህብረተሰቡ በመድረክና በሚዲያ እንዲሁም ቤት ለቤት ግንዛቤ አየተሰጠ መሆኑን በመጥቀስ ፍትህ ቢሮ በርካታ ህጎች የሕግ ረቂቆች በጥናት ተመርኩዞ የሕብረተሰቡን ችግር በሚፈታ መልኩ መስራት መቻሉን አንስቷል።
የፍትሕ ቢሮ ምክትል ሀላፊና የሕግ ጉዳዮች ክርክር ዘርፍ ሀላፊ በአካል ጉዳተኞች መብት ጥበቃና ከክርክር ጋር በተያያዘ ለተነሱት ጥያቄዎች ምላሽ በመስጠት ፍትህ ቢሮ በቅንጅታዊ አሰራር በ9 ወራት ውስጥ የተሰራ ስራ በጣም ከፍተኛ እንደሆነ በመግለጽ የሪፎርም እንቅስቃሴ ፣ ሜጋ ፕሮጀክቶች፣ ኮሪደር ልማት ላይ የቢሮ ሚና፣ ስራ ፈጠራ እንዳይስተጓጎል ትኩረት ተሰጥተው እየተሰራ መሆኑን አብራርተዋል፡፡
የውይይቱ ተሰታፊዎች የዘጠኝ ወራት ጠንካራ ስራዎች መሸራታቸውንና ሪፖርቱ ስራዎቹን በሚገልጽ መልኩ ተጠምሮ የተዘጋጀ መሆኑን ጠቅስው ሊስተካከሉ በሚገቡ ጉዳዮች ላይ ሀሳብ አስተያየቶች ሰንዝረዋሉ።
በመጨረሻም የቢሮው ኃላፊ አቶ ተክሌ በዛብህ በማጠቃለያ ንግግራቸው በቀሩት ወራት በቅንጅት በመስራት የመንግስትና የህዝብ መብትና ጥቅም በማስጠበቅ አፈጻጸማችን ሙሉ ማድረግ ይጠበቅብናል በሚል አንክሮ ተጠቃልሏል፡፡
ሚያዝያ 30/2017 ዓ.ም
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.