
በስልጠና ጽሁፍ አቀራረብ እና በማንዋል አዘገጃጀት በሚል ርዕስ ስልጠና ተሰጠ፡፡
የኢዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ የሕግ ስርጸትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት በማዕከል እና በክ/ከተማ ደረጃ ለሚገኙ የስርጸት ዐቃቢ ሕጎች ስልጠናው ተሰጥቷል፡፡
ስልጠናውን የሰጡት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ የህግ ጥናት ምርምር እና ማርቀቅ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጀማል ሳላህ በስልጠና ጽሁፍ አቀራረብ እና በፓወር ፖይንት ስላይድ አዘገጃጀት በሚል ርዕስ ዙርያ ስልጠናውን ሰጥተዋል፡፡
ስልጠና ለመስጠት ሲታሰብ በቂ ዝግጅት በማድረግ በራስ መተማመን ከፍ እንዲል ማድረግ ፣ ታዳሚውን ከመጀመሪያ ጀምሮ እስከመጨረሻ ድረስ ስልጠናውን በትኩረት የሚከታተል እንዲሆን እና የንግግር አቀራረቦች ልምምድ በማድረግ የሕግ ስርጸት ስልጠና ላይ የሚካፈለው ታዳሚ ከስልጠናው በቂ ግንዛቤ አግኝቶ ተግባር ላይ እንዲያውለው በማድረግ በስልጠና አቀራረብ ላይ በቂ እውቀት ሊኖረን ይገባል ሲሉ ገልጸዋል፡፡
በመጨረሻም የስልጠናው ተሳታፊዎቹ ከስልጠናው ሰፊ ግንዛቤ አግኝተናል ብለው በማመስገን በተሰጡት ጥያቄዎች ላይ አቶ ጀማል ምልሽ በመስጠት ስልጠናው ተጠናቋል፡፡
08/ግንቦት/2017
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.